Translation is not possible.

ሙናፊቅ በሙስሊሞች ላይ በእጅጉ ሸረኛ ነው!!

‏••══ ༻✿༺══ ••

ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-

«ሙናፊቆች በሙስሊሙ ላይ እጅግ በጣም አደገኞች (ሸረኞች) ናቸው!። የመልካም ነገር ባለቤቶችን ሲመለከቱ ይጣቀሱባቸዋል። አንዳንድ ችግሮች (ጉድለቶች) ያሉባቸውን ሰዎች ሲመለከቱ ያነውሯቸዋል። ሙናፊቅ ከአላህ ባሪያዎቹ በእጅጉ ቆሻሻና ፀያፍ ባሪያ ነው። ከእሳትም በመጨረሻው አዘቅት ውስጥ ነው!።

ሙናፊቆች በዚህ ዘመናችን የመልካም ነገር ባለቤቶችን ወደ አላህ የሚጣሩ ሰዎችን፣ በመልካም የሚያዙና ከተወገዘ ነገር የሚከለክሉ ሰዎችን ሲመለከቱ ራሳቸውን የሚያልቁ (ከፍ ከፍ) የሚያደርጉ፣ እነዚህ አጥባቂዎች፣ ኡሱሊዮች፣ ረጅዒዮች… እያሉ የመሳሰሉ ስሞችን በመጥቀስ ይወርፏቸዋል።

ይህ ሁሉ ነገር በሙሉ በመልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን ከነበሩ ሙናፊቆች እስከዚህ ጊዜያችን ድረስ የወረሱት ነው።

እኛ ዘንድ ሙናፊቅ የለም አትበሉ!። ይልቅ እኛ ዘንድ ሙናፊቆች አሉ፣ ለነሱም ብዙ አላማዎች አሉዋቸው።»

[ሸርህ ሪያዱ ሷሊሂን ከ21ኛው የከዕብ ሀዲስ ማብራሪያ የተወሰደ]  

✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://telegram.me/IbnShifa

https://telegram.me/IbnShifa

Send as a message
Share on my page
Share in the group