Translation is not possible.

★彡 ጀነትና ፀጋዎቿ 彡★

ቆየት ካሉት የሸይኽ አብዱልሀሚድ ምክሮች

በውስጡ ከተዳሰሱት ጭብጠ ሀሳቦች

✔️የጀነትና የጀሀነም ጠቅላላ ትርጓሜ

✔️የጀነት አይነቶችና የጀሀነም አይነቶ

✔️የጀነት ፀጋዎችና የጀሀነም አስፈሪ ገፅታዎች

✔️የተለያዩ አንጃዎች በጀነትና ጀሀነም ላይ ያላቸው አቋም

ቅምሻ

💥ጀሀነም ጥልቀቷ ከጀሀነም ጫፍ ላይ ሆኖ ድንጋይ ቢወረወር ለመመምዘግዘግ 70,000 አመት ይፈጅበታል በዚህም የጀሀነምን አስፈሪነት እንገነዘባለን

💥ጀነት የገቡ ሰዎች

-አያረጁም

-አይሞቱም

-አይታመሙም

-ሀሳብ ጭንቀት ትካዜ የለም

-ሽንት ሰገራ ንፍጥ አክታ የለም

-ራበኝ ጠማኝ ሆዴን ነፍኝ ቆረጠኝ ፈለጠኝ የለም

-ደም ግፊት ኤች አይቪ ተቅማጥ ባክቴሪያ ኮሮና የሚባል ነገር የለም

-እንደ ዱንያ ደበርሽኝ ደበርከኝ አረጀህ አረጀሽ ፈታሀኝ ፈታሁሽ የለም በፀጋዎች የተንበሸበሸችው ተናፋቂዋ ሀገር ጀነት

💥የጀነት ሴቶች-ሁሌም ድንግል ናቸው-እንደ ሰጎን እንቁላል የፀዱ-አይናቸውን በባላቸው የሰበሩ ሁሌም ባሌ ባሌ የሚሉ-አይናቸው ሰፋፊ የአይናቸው ነጫጩና ጥቁሩ ክፍል የደመቀ

💥ጀነት ውስጥ ባል ፊቱን በሚስቱ ጉበት ያያል ሚስቱም በባሏ ጉበት ታያለች

💥የጀነት ሴት አንድ ጊዜ ወደ ዱንያ እትፍ ብትል ዱንያን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በመልካም መአዛ ታውደዋለች

Send as a message
Share on my page
Share in the group