Translation is not possible.

«ይህ ይሁን ምርጫሽ»

➭➭➭➭➭➭➭➭➭

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

መልካም ተናጋሪ አንደበቱ እርቱ፣

ቁጭ ብሎ የቀራ በግዜ በወቅቱ፣

ኢልምን የተማረ በወጣትነቱ፣

ዝርክርክ ያልሆነ ለዲን ለእምነቱ፣

አለሁ ብሎ እሚቆም ለተዉሂድ ለሱና፣

በዉቀት የሚናገር ቆራጥና ጀግና፣

ለቢድዓ ሰዎች የሆነ ገናና፣

ከዉሸት የራቀ ለእዉነት ያደረ፣

በተዉሂድ ጉዳይ ላይ ያልተደራደረ፣

የተውሂድ የሱና ጠባቂ የሚሆን

ካዘዙበት ሁሌም የሚሞሏ ቃሉን

ጠማማውን ሁሉ በሁጃ አንበርካኪ፣

በጣፋጭ አንደበት እውነትን ሰባኪ፣

ከጠላቶች ሴራ ቃሉ ጋሻ ሁኖ፣

በደሊል ሲናገር ሰው ሁሉ አምኖ፣

አንተን የሚዘምር በጧትም በማታ፣

ሰዎች ካልበዙበት ጭር ካለ ቦታ፣

ሀጥያቱን አስቦ የሚያለቅሰውን፣

ባሪያ በመሆኑ እሚደሰተውን፣

አሏህን በማዉሳት ነፍሱን ያጠረዉን፣

አይኑን ላክ አድርጎ ወደ ግዙፍ ሰማይ፣

እንባውን ዘርግፎ በሰውነቱ ላይ፣

እባክህ የሚልህን ጭቀቱን እንድ ታይ፣

በጠፊዋ አለምም የሚታገል ለምነቱ፣

ለተውሂድ ለሱና የሚሆን መሰዋቱ፣

ሸሂድ ሁኖ የሚሞት የሚሆን ምኞቱ፣

እዉነት ተናገሪ በተግባር በእምነቱ፣

ከመረጥሽስ አይቀር እደዚህ አይነቱ፣

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

Řihu Islamic post

Řihu Islamic post

Send as a message
Share on my page
Share in the group