Translation is not possible.

ካስማ ኢስላማዊ ድርጅት/ Kasma Islamic Organization

ዛውያዎችንና ሐሪማዎችን ለመርዳት የተዘጋጀ ፕሮጀክት አካል የመሆን ጥሪ

ሀገራችን ኢትዮጲያ ከጥንት ጀምሮ እጅግ የሚያኮሩ እና በእስልምና ታሪክ የማይረሱ እስልምናን ያስተማሩ ለብዙዎች አርአያ የሚሆኑ መሻይኾች እና የእውቀት ማእከላት ሐሪማዎች መገኛ መሆኗ ይታወቃል። ኢስላምን ለትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር አበርክቷቸው እጅግ የገዘፈና የማይተካ ነው፡፡

አሁን አሁን እነዚህ እንቁና አብሪ ከዋክብት እንዲሁም የከዋክብቱ መናገሻ ሀሪማዎች ብርሀናቸው በዘርፈ ብዙ ችግሮች እየደበዘዘ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ችግሮች መካከል ጥልቅ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር ዋነኛውና አሳሳቢ ቸግር ሲሆን በካስማ ኢስላማዊ ድርጅት ተነሳሽነትና አስተባባሪነት “ ውለታ እንደዋዛ” በሚል መሪ ቃል ችግሮችን በተቻለ አቅም ሁሉ እንቅስቃሴ መጀመራችን ይታወቃል፡፡

ሐሪማዎችንና ዛውያዎችን እንመግብ፣ ሀሪማዎችንና ዛውያዎችን እናልብስ በሚል ከ ህዳር 03/2016 ዓል ጀምሮ ፕሮጀክት ይፋ በማድረግ ወደ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከላይ የዘረዘርናቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም ሀሪማዎች አሁን ያሉባቸውን አንገብጋቢ የምግብ፣ የልብስና የትም/ት ቁሳቁስ ችግሮች በተቻለ ፍጥነት ለመፍታት ታስቦ የተቀረጸና ወደተግባር የገባ ፕሮጀክት ነው፡፡ በመሆኑም እርሶ የዚህን መልካም ተግባር አካል በመሆን የበኩሎትን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪ እያቀረብን የተጠቃሚውና የድጋፍ አይነቶች በፓኬጅ ተከፋፍሎ ቀርቧል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች:

በዚህ ፕሮጀክት በ 50 ሀሪማዎች ዉስጥ ያሉ መሻይኾች ደረሶችና ኻዲሞች በድምሩ 12,550 የሐሪማ ቤተሰቦች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሐሪማ ዙሪያ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አጠቃላይ የሀገራችን ሙስሊሞች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለድጋፍ የሚያስፈልጉ ግብአቶች በአይነት እና በጥሬ ገንዘብ የሚሆን ሲሆን

 ምግብና ምግብ ነክ ግብአቶች

 የልብስ ፣ የጫማና ተያያዥ ግብአቶች

 ኪታብና ሌሎች የትም/ት ቁሳቁስ ግብአቶች

በአይነት ማሰባሰቢያ ማእከሎች:

አዲስ አባባ:

1, ፍል ውሀ መስጅድ 2, ቤቴል መስጅድ 3, ቄራ መስጅድ ሲሆኑ ቀሪ ማእከላትን በሂደት እናሳውቃለን

ክፍለ ሀገር:

ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ ኸሚሴ፣ ሰመራ፣ ሎጊያ፣ ሻሸመኔ፣ ዲላ እና ሃላባ። ሌሎችን በሂደት እናሳውቃለን

ፕሮጀክቱ በዋናነት በአይነት ቁሳቁሶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን ምናልባት በካሽ ማበርከት ከተፈለገ የ1 ደረሳ የወር ፓኬጅ 1000 ብር፣ የአንድ ሸይኽ የወር ፓኬጅ 5000 ብር በመሆኑ በሚከተሉት የካስማ ኢስላማዊ ድርጅት የባንክ ቁጥሮች፣ ጎፈንድሚ፣ ካሽአፕ እና ዜላ አበርክቶዎትን ሊልኩ ይችላሉ።

1 ዘምዘም ባንክ ፡ 0015172010301

2 ሂጅራ ባንክ፡ 1000013130001

3 ኢ/ ን/ ባንክ፡ 1000517781178

4 አቢሲንያ ባንክ፡ 159957519

5 ኮኦፕሬቲቭ ባንክ ፡ 1023500155737

6 የጎፈንድሚ አድራሻ: https://gofund.me/738dfca1

Cashapp and Zelle: 7035086164

ለበለጠ መረጃ:

0970707011|| 0938383802 || 0904593982

#ውለታ_እንደዋዛ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group