Translation is not possible.

⇘አግባኝ⁉️

↳ወዳጆቼ …ሴት ልጁ ወንድን ልጁ እንጋባ ብላ ጥያቄ ማቅረቧ…  ቅሌት አይደለም፣ መውረድም፣ መቅለልም መዋረድም አይደለም፣ ሐያእ ማጣትም አይደለም፡፡ ሐያእ ማለት ሐቅን መሸሽ ማለት አይደለም፡፡  መውደድም ወንጀል አይደለማ፡፡ ለወደደ ሰው መድሃኒቱ ጋብቻ ነዋ፡፡ 

.  

∆እንዳውም እኔ በናንተ(በሴቶች)ቦታ ብሆን…መንፈሳዊ ሕይወቱ ከሳበኝ፣ ታማኝነቱ፣ ኢማኑና ለዲን ያለው ትጋቱ ከማረከኝ … ለምን ብዬ ነው የማፍረው እጠይቀዋለሁ፡፡

እጠይቀዋለሁ፣ ሐሳቤ መልካም ነውና፣ ዓላማዬ ትልቅ ነውና፣ የዉስጤን አምላኬ ያውቃልና እጠይቀዋለሁ፣ ምኞቴ በጎ ነውና እጠይቀዋለሁ፡፡ ብጠይቀው ምንድነው ጥፋቴ!፡፡ ባማክረውና ጥቅሙ የጋራችን ነው ብለው የት ላይ ነው ክፋቴ!፡፡ እሱን በማሰቤ ምንድነው ኃጢኣቴ፡፡ አትጠይቁ የሚል አስተምህሮ አለ እንዴ!፡፡ ለሚጠቅም ነገር መሽቀዳደም ጠቃሚ አይደለም እንዴ! እናታችን ኸዲጃ ነቢዩን የመሰለ ታላቅ ሰው ከእጇ ያስገባችው ጠይቃ አይደለም እንዴ!! ሆ …

♨ስንቱ ሐራም ፍለጋ ብሎ ከቦሌ እሰከ ጉለሌ እየሄደ አይደለም እንዴ! እኔሰ ለሐላሉ ምን አሳፈረኝ?፤ እናም እጠይቀዋለሁ … ቢሳካ መልካም ነው፣ ባይሳካም አይከፋኝም፡፡ እንቢ ተባልኩ ብዬም አልሸማቀቅም፡፡ የሆነው ሁሉ አላህ ያለው ነውና፡፡ ለወንጀል አይደለም የጠየቅኩት፡፡ ለዝሙት አይደለም ያሰብኩት፡፡ እና አልፈራም፣ አላፍርም …. እጠይቀዋለሁ።

⇨ግን ያኡኽታህ ጠይቂው ብሎኛል ብለሽ ስለወደድሽው ብቻ ሳይሆን የምትጠይቂው… አስቦኝ ይሆናል ብለሽ ካሰብሽ፣ ሰው እንደሌለው ከገመትሽ፣ ለኔ ጥሩ አመለካከት አለው ብለሽ ካስተዋልሽ፣ አብሮ የሚሄድ ቀለም አለን ብለሽ ካሰላሰልሽ .. 

🎋ደሞ የሚኮራውንና የሚያስወራውን አይደለም የምጠይቂው፡፡ ኋላ ላይ ‹ጠይቃኝ፣ ወትውታኝ፣ አቻኩላኝ፣ መቆም መቀመጥ ነስታኝ፣ መግባት መውጣት ከልክላኝ … እኮ ነው ያገባኋት› ብሎ ሊመፃደቅ ይችላል ብለሽ የገመትሽውን  አይደለም የምጠይቂው፡፡

🌷እንደዚህ ካልሆነ ግን_የምሬን ነው የምልሽ  ዐይንሽን በጨው አጥበሽም ቢሆን ሀላልሽ አድርጊው፡፡  አራት ነጥብ¡።

⇨“የኔ አመለካከት ነው እህቶቼ! የናንተን አላውቅም!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group