6 month Translate
Translation is not possible.

አንድ ጊዜ ነብዩላህ ሙሳ (አለይሂሰላም) አላህን

"ከፍጡራኖችህ የምትረሳው የለም እንዴ?" ብለው ጠየቁት።

አላህም እንዲህ አዘዛቸው:—(ያሙሳ አጠገብህ ያለውን ድንጋይ ምታው) አላቸው።

ሲመቱት ለሁለት ተከፍሎ ከውስጡ ሌላ ድንጋይ አለ።

(አሁንም ምታው::)ሲመቱት ከዛም ድንጋይ ውስጥ ሌላ ድንጋይ።

ለሶስተኛ ጊዜ (ምታው) አላቸው። ያኔ

ሲመቱት ከውስጥ አንዲት ነፍሳት ቁጭ ብላ አረንጓዴ እፅዋትስትመገብ ተመለከቱ።

አላህም የዛችን እንስሳ ድምፅ ለነብዩላህ

ሙሳ አለይሂ ሰላም አሰማቸው።

እንዲህ አለች:–(በዚ ሶስት ጨለማ ውስጥ ለሚረዝቀኝ ጌታ ሁሌም ለማይረሳኝ ጌታ አላህ ጥራት ይገባው።) ስትል ሰሟት።

ሱብሀነከ ረቢ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group