Translation is not possible.

😢😢😢

እማ ቦምብ ሲመታኝ ወድያው ነው የሚ*ገለኝ ወይስ በጣም እያመመኝ ነው የምሞተው? ስሞትስ ብቻዬን ነው የምሞተው ? አይ ሁላችንም አንድ ላይ ነው የምንሞተው የኔ ልጅ።

...

ጁሪ ተጨዋች ሳቂታ፣ ሁሌም በጩኸቷ ቤት የምታደምቅ ልጅ ነበረች፣ ከወ*ረ*ራው በኃላ ግን ምግብ አትበላም እንደ ድሮ፣ ያ ሁላ ሳቅ ጨዋታ የለም፣ እናቷ የድሮ ትዝታዎችን እያነሳች ለማጫወት ብትሞክርም ጁሪ በትካዜ ከመዋጥ ውጪ ከእናቷ ጋር መቦረቅ መጫወት ካቆመች ሰነባበተች፣ ጦ*ርነቱ ካበቃ በኃላ መጀመርያ እንዳደርግልሽ የምትፈልጊው ነገር ምንድነው ? ተብላ በእናቷ ስትጠየቅ... ምንም ነገር አልፈልግም ፣ ይሄ ቦምብ ብቻ ይቁምልኝ፣ሌላ ምንም አልፈልግም። እሱን ብቻ ነው የምፈልገው ....

...

ወደ ደቡባዊ ስፍራ እንድንሰደድ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ወደ ደቡባዊ ጋዛ መሄጃ ጎዳናው ሁሉ አስክሬን ነው (ለስደት የሚወጡ ሰዎች መንገድ ላይ በቦምብ ዒላማ ተደርገው ተገለዋል)፣ አስክሬን ማንሳት ስለተከለከለ ጎዳናው ሁሉ በወዳደቁ አስክሬን የተሞላ ነው። መንገድ ላይ በቦምብ የመመታቱን ዕድል ተቋቁሜ እንኳን ጉዞ ብጀምር ልጄን በነዚህ አስክሬን መሃል ይዤ መራመድ እንዴት ይቻለኛል ? ...

...

ይህ የአልጀዚራ ጋዜጠኛዋ ዩምና አል ሰዒድ እና የልጇ ጁሪ አሁናዊ ተጨባጭ ነው ፣ በህይወት ተርፎ መቆየት ከቻሉ ደሞ ለነገ በራሷ ተሰንዶ ሊቀመጥ የሚችልና በሩዋንዳዋ ኢማኩሌ ኢሊባጊዛ 'ለወሬ ነጋሪ መትረፍ' መፃህፍት ተርታ የሚሰለፍ የዘ*ር ማ*ጥፋት ታሪክ ነው ። ከነ ልጇ አትርፎ ለዛ መብቃቱን ካደላቸው...

Send as a message
Share on my page
Share in the group