Translation is not possible.
⭕️ ምንኛ ያማረች ምክር‼
 
🛑 አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር!
 
⭕️ የምትወዴውን ሰው ማሞገስ አታብዛ፣
⭕️ ጌታውን ከማይታዘዝ ሰው ጋር አትጓዝ፣
⭕️ ቁጭ ስትል ሰዎችን አትማ፣
 
⭕️ በራሱ ጊዜ ከአንተ የራቀን ጓዴኛ ለመቅረብ አትሯሯጥ፣
 
⭕️ ራስህን አታቅል፥ አትኩራ፣
⭕️ እጅግም አትለሳለስ፥ እጅግም አትንጠባረር፣
 
⭕️ እውነቱን የሚያወራ ሰው በብዛት አይምልም፥ ታማኝ ሰው ራሱን መልካም አድርጎ አይስልም፣
 
⭕️ ሥራውን ለአላህ ብሎ የሚሠራ ሰው ኋላ ላይ አይጸጸትም፣
 
⭕️ ቸር ሰው አይመጻደቅም፣
⭕️ ራስህን ሁን፥ ሌሎች እንዴሚፈልጉት አትሁን፣
 
⭕️ ሰዎችን ማክበርህ የሆነ የምትፈልግባቸው ጉዳይ አለ ማለት አይደለም። ስለ ዲንህና አስተዳዴግህ ልታስተምራቸው ጅማሮ እንጅ፣
 
⭕️ አክብር → ትከበራለህ!
 
⭕️ በጸባይህ ውብ ሁን!
⭕️ ባለህ ተብቃቃ፥ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትልቅ ሁን።
 
⭕️ ከኋላህ ሆኖ ስለአንተ ወዴሚያወራ ሰው አትመልከት። ምክንያቱም እርሱ በመሠረቱ ከኋላህ እንጅ ከፊት ለፊትህ አይዴለም።
 
⭕️ ከቁርኣን ምን ያክል እንደምትሸመድድና እንዴምትቀራ ለሰዎች አትንገራቸው። ይልቁንም በአንተ ውሰጥ ቁርኣንን እንዲያዩ አድርጋቸው።
 
⭕️ የተራበን አብላ፣ የተራቆተን አልብስ፣ እርዳታህን የሚሻን አግዝ፣ ለየቲም እዘን፣ የበደለህን እለፈው፣ ለወላጆችህ መልካም ዋል፣ ለሁሉም ፈገግ በል!
 
⭕️ ቁም ነገሩ ከቁርኣን ምን ያክል ዴርሰሃል ወይንም ሸምዴሃል ሳይሆን፤ ቁርኣን በአንተ ውስጥ የት ዴርሷል የሚለው ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group