1 year Translate
Translation is not possible.

ቂያማህ ሩቅ አይደለም

ከቂያማህ ምልክቶች ትንንሾቹ አብዛኛዎቹ ታይተዋል። አሁን የቀሩት ትልልቆቹ ናቸው። ትልልቆቹ አንዴ መከሰት ከጀመሩ ደግሞ ነቢዩ ﷺ «ልክ እንደተበጠሰ ዶቃ ናቸው» ባሉት መሰረት በተከታታይ የሚወድቁ በመሆናቸው ምናልባት የአንድ ሰው ዕድሜም ላይፈጁ ይችላሉ።

♦️ ከትልልቆቹ ምልክቶች የመጀመሪያው የኸሊፋው መህዲ መነሳት ነው። እሱም ዓለምን በሸሪዓ የሚገዛ ሲሆን የሚቆየው 7 ዓመት ነው።

(ኢብን ማጃህ 4039)

♦️ ቀጥሎ ደጃል የሚነሳ ሲሆን እሱም የሚቆየው ለ40 ቀናት ወይም ለ1 ዓመት ከሁለት ወር ነው።

♦️ ከዚያም ዒሳ (ዐሰ) የሚወርድ ሲሆን እሱም የሚቆዬው ለ40 ዓመት ነው። ሆኖም አርባ የተባለው ቀድሞ የኖረውን 33 ዓመት ጨምሮ ስለሆነ 7 ዓመት ብቻ ነው የሚሉ አሉ።

♦️ በዚህ መሃል የዕጁጅና መዕጁጅ የሚነሱ ሲሆን እነሱም ከ7 ዓመት በኋላ ይጠፋሉ።

(ቲርሚዚይ 2240)

♦️ ከዚያም ከዒሳ (ዕ) ህልፈት 7 ዓመት በኋላ ነፋስ ከምስራቅ ትነሳና ሁሉንም ሙስሊሞች ትገድላለች።

(ሪያዱ ሳሊህን 1810)

♦️ በመጨረሻም ሙሽሪኮች ብቻ አላህ ለሚሻው ጊዜ ከቆዩ በኋላ ቂያማህ ይቆማል።

🔵 በአጠቃላይ ከላይ ያሉትን ዓመታት ስንደምራቸው የአንድ ሰው ዕድሜ ቢሆኑ ነው። ይህ ማለት በዚሁ በእኛ ዘመን ትልልቆቹ ምልክቶች መከሰት ከጀመሩ እኛው ላይ ይፈፀማል ማለት ነው።

እናም በሩቅ ዘመን የሚከሰት አድርገን አንሰበው ለማለት ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group