Translation is not possible.
⚜ ኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ ረሂመሁላህ ከነበረው መተናነተስ ፦
በአንድ አጋጣሚ ሊሰግድ ወደ መስጂድ ይገባል ። ወቅቱም ምሽት ስለነበረ ከጨለማው  የተነሳ ኡመር ሳያስበው ተኝቶ የነበረን ሰው እግር ይረግጣል ።
ሰውዬውም በመበሳጨት ለኡመር " አንተ አህያ ነህ እንዴ ⁉️ " ይለዋል
ኡመርም ተረጋግቶ " አይደለሁም እኔ ኡመር ነኝ "ይለዋል
ኡመር ጋር የነበረ ሰው ተገርሞ " ያ አሚረል ሙዕሚኒን ! አህያ ብሎ እኮ ሰደበህ " ይለዋል
ኡመር እንዲህ ብሎ መለሰለት ፦
" አህያ ነህ እኮ አላለኝም…  አህያ ነህ እንዴ
ብሎ ጠየቀኝ መለስኩለት !! "
------ ምንኛ ያማረ ትዉልድ ነበር በአላህ!
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group