Translation is not possible.

ጋዛ አነቃችን (3)

🚩 ፍልስጤምን ከባህሯ እስከ ወንዟ ድረስ ነፃ ማውጣት እንደሚቻልና በዚህ ወቅት የሆነው ነገር ሁሉ ለሚመጣው ትልቅ ነገር ጥቂት ልምምድ እንጂ ሌላ አለመሆኑን ጋዛ አስተምራናለች

🚩 አንድን ነገር ማሳካት የፈለገ ሰው ማድረግ እንደሚችልና ጉዳዩ ከአቅም ጋር የተገናኘ ሳይሆን ከፍላጎት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ጋዛ ምሳሌ መሆን ችላለች። ለበርካታ ዓመታት በጽዮናዊያን ከበባ ውስጥ ያለችው ይህች እፍኝ የማትሞላ ከተማ የራሷን መሳሪያ እያመረተች ከወራሪዎች ጋር አንገት ለአንገት ልትተናነቅ እንደምትችልና በውጤቱም ከጠላቶቿ በፊት ወዳጆቿ ሊገረሙ እንደሚችሉ አስቦ የሚያውቅ ማን ነበር ?

🚩 ልጆች በችግር ቀለበት ውስጥ ካለፉ ከዘመናቸው እና ከእኩዮቻቸው በፊት አድገው የጀግንነት ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻላቸው ጋዛ ፍንጭ ሰጥታለች። በእምነታቸው ጸንተው ጉድጓድ ውስጥ በሚንቀለቀል እሳት ውስጥ በቁማቸው የተቃጠሉ አማኝ ህዝቦችን (አስሐበል ኡኽዱድ ) በህልፈቱ እንዳነቃቃው ህጻን ጋዛዊያንም ለሌሎች አርአያ ሆነዋል። ይህ ሃይማኖት ደም ህያው ሲያደርገው፤ እንባ ያጠፋዋል። እንባችሁን እያበሳችሁ የነገውን ሰማዕት ኮትኮቱ።

🚩 እምነት ተግባር እንጂ ዲስኩር እንዳልሆነ ከጋዛዊያን ቀስመናል። እንደ ዶፍ እየወረደባቸው ያለውን መከራ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ አንዳቸውም የአላህን ፍርድ ሲያማርሩ አላየናቸውም። የወዳጆቻቸውን የተበጣጠሰ ሰውነት እየሰበሰቡና በእጆቻቸው እንባቸውን እያበሱ አላህን ከማመስገን ቅንጣት አልቦዘኑም። እምነታቸው ልባቸውን ሞልቶ ከአካሎቻቸው በላይ ፈሰሰ።

د. أدهم شرقاوي

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group