1 year Translate
Translation is not possible.

ለፈገግታዎ

ህፃኑ «ጠለዐል በድሩ ዐለይና» የሚለውን ነሺዳ እያቀነቀነ ወደ መጻዳጃ ቤት ገባ። የልጁን ድርጊት የተመለከተው አባት የመፀዳጃ ቤቱን በር ከፍቶ በመግባት ልጁን መታው። ህፃኑ ክፉኛ አለቀሰ። የአብራኳ ክፋይ መመታቱን ያስተዋለችው እናትም ባለቤቷን «ለመሆኑ ልጁን የመታኸው ለምንድን ነው?» በማለት ጠየቀችው። ባለቤቷም «መጸዳጃ ቤት ውስጥ ሆኖ ቁርአን ሲቀራ ታዲያ ምን እንዳደርገው ታስቢያለሽ?» በማለት ምላሽ ሰጣት። የህጻኑ እናትም «ሲያቀነቅን የነበረው እኮ ቁርአን ሳይሆን የዐረብኛ ግጥም ነው» በማለት አስረዳችው። በዚህ ጊዜ የአባትዬው እንባ እንደ ደራሽ ወንዝ ድንገት ጎረፈ። ሚስቱም «ምን ሆነህ ነው እንዲህ ስቅስቅ ብለህ የምታለቅሰው?» ብላ ብትጠይቀው ጊዜ:-

«ላለፉት 30 ዓመታት ይህን ግጥም ሰላት ውስጥ ስቀራው ነበር» ብሏት አረፈ።

«أخبار الحمقى والغفلين»

ከተሰኘው የኢብነል ጀውዚ መጽሃፍ የተቀነጨበ

Send as a message
Share on my page
Share in the group