ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት በእስራኤል ጽንፈኞች ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠየቀች።
የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዴክሮ በፍልስጤማውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት የሚያበረታ “አክራሪ” እስራኤላውያንን የአውሮፓ ህብረት መከልከል እንዳለበት ተናግረዋል። በተወረረችው ዌስት ባንክ ፍልስጤማውያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመጥቀስ በእንደዚህ አይነት አመፅ "ጽንፈኞች" ላይ እርምጃ አለመወሰዱ "ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።
"አገራችን ከባድ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ፣ ለምሳሌ በዌስት ባንክ ውስጥ ሁከት የሚፈጥሩ ወደ አገራችን እና ወደ አውሮፓ ህብረት እንዳይገቡ መከልከላቸውን ማረጋገጥ አለባት" ሲሉ ዴክሮ ለቤልጂየም ፓርላማ ተናግረዋል። "ምንም ማድረግ በማይችል እና በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በሚኖር የፍልስጠየም ህዝብ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጥቃት እንዲፈፀም የሚጠይቅ ሚኒስትር" ጨምሮ አመፅ በሚያባሱ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።
©@ethmohammedia ከ Asharq al awsat

©የሙሐመድ ትውልድ ከ Asharq al awsat