1 year Translate
Translation is not possible.

ጋዛ የአለምን ገመና ያጋለጠ የሁላችን ጓዳ!

**********************************

___የአቅል አይምሮ ትዝብት ለ RRN05_

አቅም የለሹ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ማለት የቻሉት ነገር ቢኖር "የሰባዊ እርዳታ ለጋዛ ነዋሪዎች ቢወሰንም እስራኤል ድብደባዋን የባሰ ቀጥላበታለች፡፡ ይህም ተቀባይነት የለዉም! " ማለትን ነው፡፡ ይህንንም ማለታቸው እጅግ ፍትሃዊና ጀግና እያሰኛቸው ሲሆን በጺዮናዊያንና አጋዦቻቸው ዘንድ ደግሞ ጥርስ አስነክሶባቸዋል፡፡

በርግጥ ተመድ ማነው? አቅሙስ ምን ያህል ነው? ማን ሲፈቅድለት ነው አንበሳ፣ ማን እምቢ ሲለው ነው ድመት የሚሆነው? በርግጥ አለም አቀፍ ተቋማት ማናቸው? አቅማቸዉስ ምን ያህል ነው? አለም አቀፍ ሚድያዎች በርግጥ ማንናቸው_? አቅማቸዉስ? ሚናቸዉና ግልጋሎታቸዉስ ለማን ነው?

ይህ ሁሉ የሚያሳየው ከአለማችን ምድራዊ ህግ በላይ የሆኑ አካላት በዋናነት ጺዮናዊያን ሲሆኑ ቀጥሎ አሜሪካን ናት ሊያስብል የሚችለው፡፡ አንዳንዴ ቅደም ተከተሉ ሊቀያየር ይችላል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት ሃገራት አብዛኞቹ ነጻ ሃገራት ይምሰሉ እንጂ አሜሪካ የምትለዉን ከመድገም ዉጭ እጣ ፈንታ የሌላቸው ፖለቲከኞቻቸው የህዝቦቻቸዉን አለማቀፋዊ ህሳቤ በወል እንጂ በተናጠል እንዳይቀርጹ ቀፍድደው የያዙ ናቸው፡፡

ከዚህ ዉጭ ጥቂት እንቢ ባዮች ከመኖራቸው በቀር ሌላው ለእለት ዳቦዉና ለሚሰፈርለት ቀለብ ተገዥ -ያንንም እያሰላ ተጓዥ ነው፡፡

እናም የጋዛ ጦርነት የአለምን ገበና ፍልቅቅ አድርጎ ያጋለጠ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ምናልባትም ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ conspiracy theory ነት ይበዛበታል የሚባለው አዲስ የአለም ስርዓት (New World Order) ይፈጠራል ብለን እንጠብቃለን ለማለት ነው፡፡

ይሄው ነው!

እናንተስ አለም በዚሁ መንገድ ትቀጥላለች ትላላችሁን? እንግድያው ጻፉ እና እንሞጋገት!

Send as a message
Share on my page
Share in the group