Translation is not possible.

✔ለአንድ ጎሳ (ህዝብ) ለአይሁድ ብቻ የተላኩት (ኢየሱስ ክርስቶስ ) (ማቴ 15:24)

Vs

✔ለዓለም ህዝብ የተላኩት (ነቢዩ ሙሀመድ (ሰዐወ))(ሱረቱል አል አንቢያእ:107)

የመጨረሻው የዓለም ነቢይ የሆኑት ነቢዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ግን የተላኩት በሁሉም ዘመንና ስፍራ ላሉ (ለዓለም) ህዝቦች በሙሉ መሆኑን ተናግረዋል። ቅዱስ ቁርአንም ይህንኑ ያረጋግጣል ።

"ሙሐመድ ሆይ! ለአለማት እዝነት አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም"። (ሱረቱል አል አንቢያእ:107)

ህፃናቱ እነማን ናቸውን ?

ውሾቹስ እነማን ናቸው?

በምንባቡ መሠረት ልጅቷ እስራኤላዊት ባለመሆኗ ምክንያት ኢየሱስ እምቢ ካሉ ዘንዳ ሊሰጥ የሚችለው ትርጉም ሕጻናቱ ሕዝበ ኢስራኢል ናቸው ማለት።

ውሾቹ እና አሳማዎች የተባሉት ደግሞ ከእስራኤላውያን (ከአይሁዳውያን) ነገድ ውጭ ያሉ ማንኛውም ህዝብ ወይም አሕዛብ ማለትም ከ 12ቱ የያዕቆብ ልጆች (እስራኤላዊ) ያልሆኑ ሁሉ ህዝቦች ናቸው ማለት ነው ውሾች, ቡችሎችና አሳማዎች፡፡ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮት ማለት ነው።

ስለዚህም ወንጌል በሚነግረን መሰረት ኢየሱስ ያሉት ነገር እስራኤላዊ ከሆናችሁ ብቻ

✔ከሕጻናቱ ትቆጠራላችሁ።

✘ እስራኤላዊ ካልሆናችሁ ግን ከውሾቹ ወገን ናችሁ! ማለት ነው በግልፅ ቋንቋ አለቀ።

ማስረጃ ከፈለጋቹ ይሀው☞ [የማቴዎስ ወንጌል 15 ፥ 22-26] እና [ፊልጵ 3:2) ከፍታቹ ተመልከቱና አረጋግጡ።

በተቃራኒው ግን እስልምና ሰዎችን ህፃናትና ውሾች ብሎ በሁለት መደብ አይከፍላቸውም።

ቅዱስ ቁርዓን እንዲህ ይላል:–

‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ #አላህ_ዘንድ_በላጫችሁ #በጣም_አላህን_ፈሪያችሁ_ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡›› (49:13)

@

‼አያችሁን? እስላም ሕዝቦችን ምርጦችና፤ መናኛዎች ብሎ በዘር ፣በጎሳና በብሄር መድሎ መሠረት ላይ አይከፋፍላችውም፡፡‼

ክርስትና ስለ ዘረኝነት ወይም ስለ ራሱ ጎሳ የበላይነት ሲሰብክ ተመልከቱ!

ጳውሎስ እንዲህ አለ:–

“እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ኃጢአተኞችም የሆኑ አሕዛብ አይደለንም፤”

— ገላትያ 2፥15

“አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤”

— 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥20

"ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።”

— ሐዋርያት 22፥3

“ጳውሎስ ግን፦ እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤”

— ሐዋርያት 21፥39

በእስልምና ግን ነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) እንደተናገሩት "ሁሉ ሰዎች እንደ ማበጠሪያ ጥርስ የማይበላለጡና እኩል የሆኑ መሆናቸውን ያስተምራል።

በተጨማሪም ነቢዩ (ሰዐወ) ሰው ሁሉ ከአዳም የተፈጠረና አዳም ደግሞ ከአፈር የተፈጠረ በመሆኑ አላህን በመፍራቱ ፅድቅ ስራው ብቻ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው ከሌላው ሰው በምንም የማይበላለጥ መሆኑን ተናግረዋል።

ታዲያ የትኛውን ሀይማኖት ነው የሚመርጡት?

ሰዎችን በህፃናትና በውሾች እንዲሁም በአሳማ መደብ በሁለት ምድብ የሚከፍለውን ክርስትና ሃይማኖት ወይስ የመላውን ሰው ልጅ በእኩል አይን ተመልክቶና አክብሮ የሚያስተምረውን የኢስላም ሃይማኖት?

የፈለጉትን ይምረጡና ለምርጫዎ ትክክለኛነት ሀላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለበዎት ያስታውሱ።

ይቀጥላል

Send as a message
Share on my page
Share in the group