Translation is not possible.

➡️ዱዓ አድርገን ለምንድነው አላህ የማይቀበለን?

  - ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም በበስራ ገበያ በኩል እያለፈ ሰው ወደርሱ ተሰበሰበና… " አቡ ኢስሃቅ ሆይ! ዱዓእ አድርገን ለምንድነው ተቀባይነት ያላገኘነው?" ብለው ጠየቁት

- እርሱም "ልቦቻችሁ በ10 ነገሮች ስለሞተች ነው"

ብሎ መለሰላቸው

- " ምንድ ናቸው?" ብለው ጠየቁት

- እርሱም…

1️⃣ አላህን አውቃችሁ

ሀቁን በደንብ አልተወጣችሁም

2️⃣ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) እንደምትወዱ ተናግራችሁ

ከዚያም ሱናውን መከተል ተዋችሁ

3️⃣ ቁርአንን ቀርታችሁ አልተገበራችሁትም

4️⃣ የአላህን ፀጋ እየበላችሁ አላመሰገናችሁም

5️⃣ ሸይጣን ጠላታችን ነው ብላችሁ ጓደኛው ሆናችሁ/ተስማማችሁት

6️⃣ ጀነት ሀቅ ነው ብላችሁ ለሷ አልሰራችሁም

7️⃣ እሳት ሀቅ ነው ብላችሁ ከሷ አልሸሻችሁም

8️⃣ ሞትም ሀቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተዘጋጃችሁም

9️⃣ ከእንቅልፋችሁ ተነስታችሁ የራሳችሁን ነውሮች ዘንግታችሁ በሰው ነውሮች ተጨናነቃችሁ

🔟 በነሱ ምንም ሳትማሩ ሙታኖቻችሁን ትቀበራላችሁ

ብሎ መለሰላቸው ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group