Translation is not possible.

ቀይ መስቀል የእርዳታ መኪናው በጋዛ እንደተመታ አስታወቀ‼️

አለም አቀፉ ቀይ መስቀል በደቡባዊ ጋዛ ወደሚገኘው አልቁድስ ሆስፒታል ህይወት አድን መድኃኒቶች ጭነው ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ አንዱ መኪናው እንደተመታ እና አሸከርካሪውም እንደተጎዳ አስታወቀ።

አሽከርካሪው ከሞት "በሳንቲሜትሮች" ርቀት ውስጥ ነበር ብሏል። "እውነት ለመናገር ለሰብዓዊ ረድዔት ተቋማት እርዳታ ለማድረስ ምቹ አይደለም መኖር ይቅርና" ሲሉም ከእርዳታ ጭነቱ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩት የተቋሙ የጋዛ ቢሮ ኃላፊ ዊልያም ሾምቡርግ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"መሰረታዊ የደህንነት ከለላ እና አቅርቦቶች እንፈልጋለን። ሰራተኞቻችን የምናፈራርቅበት ሁኔታም መረጋገጥ አለበት" በማለት የተናገሩት ኃላፊ ሆስፒታሎች ያላቸው ነዳጅ እንደተመናመነ እንዲሁም የሚጠጣ ውሃ ማግኘትም የእለት ተዕለት መሆኑንም ገልጸዋል።

"በጋዛ ውስጥ የትኛውም ቦታ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም" ብለዋል። ኃላፊው በደቡባዊ ጋዛ ያለውን ሁኔታ "ሰብዓዊ ጥፋት" ሲሉ ገልጸውታል።በፍርሓት የተዋጡ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ህጻናት እና አዛውንቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ በባዶ እግራቸው አይተናል። በርካቶችም ምግብ እና የሚጠጣ ውሃ ፍለጋ እየተንከራተቱ ነው ብለዋል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group