Translation is not possible.

በኢማም ማሊክ ዘመን ነው።

ባል እና ሚስት ከባድ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተው ሚስት ደረጃ ላይ ሆና ባል

ደግሞ ከታች ምድር ላይ ሆኖ ስድብ እየተቀባበሉ ነው። (ፎቅ ድሮም ነበር)

የሚስቱን የስድብ ናዳ መቋቋም የተሳነው ባል ዳግም ከዚህች ሴት ጋር አብሮ

ላለመኖር ወሰነ'ና፦‹‹ከደረጃው ከወጣሽም፣ ከደረጃው ከወረድሽም፣ ደረጃው

ላይ ቆመሽ ከቀረሽም ኒካችን ወርዷል ማለት ነው›› ብሎ ለፈትዋ እማይመች

አይነት የኒካ ፍቺ መስፈርት አስቀመጠ።

የተወሰነ ቁማ አሰላሰለች። ደረጃውን ብትወጣ ባሏ ሊፈታት ነው፤ ደረጃውን

ብትወርድም ሊፈታት ነው፤ ቆማ ብትቀርም መፈታቷ አይቀርም። አንድ ዘዴ

ዘየደች'ና ከቆመችበት ደረጃ ላይ ዘላ ባሏ ላይ ሰፈረችበት።

እሷ ካላዩ ሁና ሁለቱም ወደቁ። በሚስቱ ብልኃት የተደመመው ባል ከስር ሁኖ

እየተነፈሰ፦‹‹አቦ ፈትዋ! ወላሂ ኢማም ማሊክ ከሞቱ የመዲና ሙፍቲ (ፈትዋ

ሰጪ) ምናደርግሽ አንችን ነው››

ምንጭ፦

ﺍﻟﻤﺴﺘﻄﺮﻑ ﻓﻲ ﻛﻞ ﻓﻦ ﻣﺴﺘﻈﺮﻑ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group