ummu Fatima shared a
Translation is not possible.

ሀማስን በአለም ህዝብ ጨካኝ ለማስባል በራሷ ዜጎች ላይ የጨከነቺው እስራኤል !!

መቼም የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የአለምን አይንና ጆሮ ሰቅዞ እንደያዘ ይሄው ድፍን አንድ ወር አለፈው ። ታድያ October 7 በሀማስ የተፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት ሁሉንም ያነጋገረ ሚስጥር ሆኖ እስካሁን ቀጥሏል ።

እርግጥ ነው ሀማስ የእስራኤልን አጥር ጥሶ በርካታ ወታደሮቿን ገድሎ ከዚያ መያዦ የሆኑ ከ 250 በላይ ወታደሮችንና እስራኤላውያንን ሲቪሎችን ይዞ ተመልሷል ። ግና እውን ሀማስ ንፁሀንን በዚያ ልክ ገድሏል ወይ ? ከገደለስ ለምን እነዚህን የያዛቸውን ዜጎች እስካሁን ማቆየት ፈለገ ? ለምንስ የደከሙትን ምርኮኞች ለቀቀ የሚለው አነጋጋሪ እንደሆነ ነው ።

በተለይም የ Pink Floyd ተቋም ዋና መስራች የሆነው ሮጄር ዋተርስ " የራሷን ንፁሀን ዜጎች የጨፈጨፈቺው እራሷ እስራኤል ናት ይህንንም ያደረገቺው ሀማስን ጨካኝ አስብላ በጋዛ ላይ የምትከፍተውን ወረራ ህጋዊ ለማድረግ ነው " በማለት ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል ።

እርግጥ ነው ሀማስም በሰጠው መግለጫ አንድም ንፁሀንን አልገደልኩም የገደልኩት የእስራኤል ወታደሮችን ብቻ ነው በማለት ገልጿል ። የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ ዋና ሀላፊ ሙሀመድ ዳኢፍም " እኛ ንፁሀንን አልገደልንም የገደልነው የእስራኤል ወታደሮችን ብቻ ነው ወደዚህ ተይዘው የመጡት መያዦችም በተለያዩ ወታደሮቻችን የተያዙ ናቸው ሁኔታዎች ሲመቻቹም እንለቃቸዋለን አንድም ንፁሀንን አንገድልም " ብለዋል ።

ታዲያ 1,400 ሟች ከየት መጣ ?

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሀማስ በጥቃቱ የገደላቸው የእስራኤል ወታደሮች ብዛት ከ 400 ይልቃሉ ። በዚህም ከፍተኛ ውርደት የደረሰባት እስራኤል ጥቃቱን ለመበቀል አለም ሀማስን ጭራቅ አድርጎ እንዲያየውና ከዚያ በሗላ እስራኤል የምትወስደውን የጭካኔ እርምጃ ሁሉ ብትወስድ ተቃውሞ እንዳያየሳባት ማድረግ ነበረባት ነው ተረኩ ። ለዚህ ደግሞ ሀማስ ጭካኔን እንደፈፀመ አለም ማየት አለበት ። እናም እስራኤል የራሷ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጨከነች ይላሉ የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ። እናም የህፃን ልጅን አንገት መቅላትን ጨምሮ የጭካኔ እርምጃዎችን ወስዳ ሀማስ ፈፀመው አስባለች ነው የሚሉት ። ሀማስ ደግሞ የፈለገ ቢሆን ህፃን ልጅን አን*ገቱን አይቀላም ነው ። በርግጥ ይህኛ ሀማስ ህፃንን አን*ገቱን ቀላ የሚለው የእስራኤልን ውንጀላ ከአሜሪካ ውጭ እውነት ብሎ የተቀበለው አንድም ሀገር የለም ።

ሌላው ክርክር ደግሞ ጭራሽ እነዚህ ሁሉ ንፁሀን አልተገደሉም እስራኤል ዝም ብላ ነው ቁጥሩን የቆለለቺው የሚል ነው ። 1,400 ንፁሀን ከተገደሉ አስክሬናቸው የታለ ? የታለ የጅምላ መቃብራቸው ? የታለ የቀብር ስነስርአታቸው ? ስለምን የዚህ ሁሉ ሰው አስክሬን አልታየም ? የሚሉ ናቸው ። እነዚህኞቹ ደግሞ እስራኤል የጭካኔ እርምጃ ልትወስድ ስለተዘጋጄች ነው ይህንን ቁጥር የሰቀለቺው የሚሉት ። ሀማስ ግን የገደልኩት ወታደሮችን ብቻ ነው እንዳለ ነው ።

በርግጥ እስራኤል በዚህ አይነት ድርጊት የምትታወቅ ሀገር ነች ። የእስራኤላውያን ታሪክም እንደዚህ ነው ። የራሳቸውን ሰው ራሳቸው ገድለው በጠላታቸው ላይ ካመካኙ በሗላ ለጦርነት ምክንያት ለጭካኔያቸውም ማስረሻ ያደርጉታል ። ይህንን በነብያቶች ላይ ጭምር ፈፅመውታል ። ይህን ድርጊት ፈረንጆቹ False flag Attack ይሉታል ።

እስራኤል ይህንን ታሪክ ከዚህ በፊት ግብፅ ላይም ሞክራው ነበር ። ያኔ በ 1954 የእስራኤል ጦር አይሁዳዊያን አጥፍቶ ጠፊዎችን በማዘጋጀት የግብፅ ሀይል አስመስሎ በምእራባውያን ተቋማት ላይ ጥቃት እንዲሰነዝሩ አዘጋጅታ ግና ሳይሳካላት የተሰማሩት አይሁዳዊያን ሲሞቱ የተቀሩትንም የግብፅ ባለስልጣናት ገድለዋቸዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ የእስራኤል ምስረታ በእንደዚህ አይነት False flag attacks ጭምር የታገዘ ነበር ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group