Translation is not possible.

ጋዛ አንቅታናለች (1)

🚩 አላህ በኛ ላይ የዋለውን ስፍር ቁጥር የለሽ ጸጋ እንድናከብር ጋዛ ትልቅ ትምህርት ሰጥታናለች። በዚያች ምድር ንፁህ ውሃ መጠጣት ህልም ሆኗል። ትኩስ ዳቦ ማግኘት ስኬት ነው። ሰውነትን መታጠብ ቅንጦት ሲሆን እድሉም ከተገኘ በማልዲቭስ የባህር ዳርቻዎች ላይ እግርን ዘርግቶ ከመተኛት ጋር ይስተካከላል። ጋዛ ውስጥ በዚህ ወቅት በነዋሪው አናት ላይ ያልተደረመሰ ትንሽ ቤት ከዓለም ቤተ መንግስቶች የበለጠ ዋጋ ያለው ነው።

🚩 ሶሓቦችን መሳይ ሰዎች በመካከላችን አየኖሩ እንዳለ ጋዛ አሳይታናለች። የኻሊድ ቢን አል-ወሊድ ዘሮች የጠላትን ጦር በብርቱ እየወረሩ እንዳለ ታዝበናል። የሰዓድ ብን አቢ ወቃስ ዘሮች በቀስቶቻቸው ኢላማቸውን በትክክል እየመቱ እንደሆነ አይተናል። የዒክሪማ ዘሮች አሁንም ለሞት ቃል ኪዳን እየገቡ እንደሆነ ምስክር ሆነናል። የቃዕቃዕ ዘሮች በሠራዊቱ ውስጥ ልብን ከስፍራው በሚያነቃንቅ ድምጽ «በአሸናፊው አላህ ሥም!» እያሉ ለነጻነታቸው ሲታገሉ ሰምተናል።

🚩 ኸንሳእ እንዳልሞተችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቅጂዎቿ በመካከላችን እንደሚኖሩ ታዝበናል። በፅኑ ታግሰው እና የአላህን ውዴታ ፈልገው ልጆቻቸውን በመንገዱ ላይ አሳልፈው የሰጡ እንስቶች በመካከላችን እንዳሉ ጋዛ አሳይታናለች።

Send as a message
Share on my page
Share in the group