የዶክተር ዛኪር የፍርድ ሂደት ተጠናቀቀ፣ 320ሺ ዶላር ካሳውንም ለፍልስጤማውያን ይሁንልኝ ብሏል።
ጉዳዩ እንዲህ ነው። በአንድ ወቅት ዶክተር ዛኪር የማሌዥያ ራስገዝ አስተዳደር ወደሆነችው ፒናንግ ንግግር ያደርግ ዘንድ ተጋብዞ ይሄዳል።
በወቅቱ አንድ መቶ ሺ ህዝብ ታድሞ በቀረበው ንግግር ተደስቶ ፕሮግራሙ ይጠናቀቃል። ከዚያ በዃላ ሁኔታው ያልተዋጠላቸው በሃገሪቱ መንግስታዊ ስርአት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ዛኪርን አሸባሪ፣ የጥላቻ ንግግር ሰባኪ በሚል መውቀስና መስደብ ጀመሩ። ዛኪር ስለጉዳዩ ሲያብራራ እንዲህ ይላል
«አምስት ናቸው። ሳጣራ ሁሉም ፖለቲከኞች ሲሆኑ የህንድ ዝርያ ያላቸው ናቸው። ይህንን ጉዳይ ዝም ማለት ስላልፈለኩ ወደ ፍርድ ቤት ሄጄ ከሰስኩኝ። ከአምስቱ አራቱ በነገሩ በመደናገጣቸው ይቀርታ በመጠየቅ ጉዳዩ እንዲዘጋ አናገሩኝ። እኔም ይቅርታ አደረኩላቸው። አንደኛው ግን የወቅቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ራማሳይ ጥላቻቸው ጥግ የደረሰ በመሆኑ የክስ ሂደቱ እንዲቀጥል አደረኩኝ።»
ዶክተር ዛኪር አሁን የሚገኘው ናይጀሪያ ነው። ሰሞኑን ከሶስት ወር በፊት በተደረገለት ግብዣ ወደ ናይጀሪያ ተጉዞ በየአካባቢው ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛል። በርካታ ሰዎችም እስልምናን በመቀበል ላይ ናቸው።
ታዲያ ያኔ ግብዣ ሲደረግለት ጠበቃው ክስ እንዳለበትና ኖቬምበር 2 ፍርድ እንዳለውና እንዳይንቀሳቀስ ይነግረዋል። ዛኪር ግን ግብዣ ተቀብያለሁና መቅረት አልችልም የሚወሰነውን እቀበላለሁ ብሎ ነበር ወደናይጀሪያ ያመራው።
ዶክተር ዛኪር ኖቬምበር 2 የነበረውን ግብዣ ተከትሎ በናይጀሪያ ንግግር ሲያደረግ የመረጠው ርእሰ ጉዳይ የፍልስጤምን ሰቆቃና የሙስሊሙን ሃላፊነት ነበር። ይህንን ንግግር እያደረገ ስለነበረው የክስ ሂደት ካብራራ በዃላ ዛሬ የፍርድ ሂደቱ ከሁለት አመት በዃላ ተጠናቀቀ፣ ዳኛውም ስሜን በማጥፋት በደል ለፈፀመብኝና ጥላቻውን ለገለፀው የቀድም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጥፋተኛ ብሎታል ሲል ገለፀ።
የፍርድ ሂደቱን ተከትሎም በ30 ቀናት ውስጥ 1ሚሊዮን 4መቶ 20ሺ የማሌዥያ ገንዘብ ወይንም 320ሺ ዶላር ለዶክተር ዛኪር ናይክ ካሳ እንኪፍል ውሳኔ ተሰጠ። 320ሺ የአሜሪካን ዶላር በኛ ሃገር በባንክ ምንዛሬ ከ16ሚሊዮን ብር በላይ ነው።
ዶክተር ዛኪር ናይክም በመድረኩ ባደረገው ንግግር ይህንን የቅጣት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለፍልስጤም እርዳታ እንዲውል መወሰኑን አሳውቋል።
ይህ ትንሹ ለወንድምና እህቶቼ የማደርገው ነው ሲል ገልፁዋል።
ዶክተር ዛኪር ከህንድ በስደት ማሌዥያ የሚኖር ሲሆን በተለያየ መንገድ ዛሬም ዳዕዋውን አስቀጥሏል። በርካታ የኢስላም ጥላቻ የተጠናወታቸው አካላት ዛሬም እሱን መክሰሳቸውና ማሳደዳቸውን አላቆሙም። እሱም ከጥሪውና የአላህን መንገድ ከማስተዋወቅ አልተወገደም።
አቡሐኒፋ - ሙሀመድ ሰዒድ