Translation is not possible.

ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተላለፉ 10 ትልላቅ የቂያማ ቀን ምልክቶች:-

1 የደጃል መምጣት !

2 የመርየም ልጅ ነብዩሏህ ኢሳ (ዐሰ) ደጃልን ለማጥፋት ከሰማይ መውረድ!!

3. የየዕጁጅ እና መዕጁጅ መምጣት !

4. በስተ ምስራቅ የ 1ከተማ መሬት መደርመስ ክስተት ማለትም ከተማዋ የት እንደገባች እስማይታወቅ ትጠፋለች። (ትሰምጣለች)

5 ደግሞ እንደዚሁ በስተ ምዕራብ አንድ ትልቅ ከተማ ተገለባብጣ ትጠፋለች።

6 ብዙ የአረብ ግዛት መሬት ይደረመሳል ሰዎች ምድር ምን ነካት?? እያሉ ይነጋገራሉ !

7 ብርቱ የሆነ ጭስ ይነሳል በሰማይ ና በምድር ይሞላዋል ለአማኞች ወረርሽኝ ሲሆን ለከሃዲዎች ቅጣት የሆነ።

8 ፀሀይ በመግቢያዋ ትወጣለች ያኔ መላኢካዎች ብዕራቸውን ያስቀምጣሉ። የተውበት በር ይዘጋል። የመልካም ስራ የመጥፎ ስራ የሁሉ ነገር መቀበያ መዝገብ ይዘጋል።

9 አንድት እንሰሳ ትወጣለች ሰዎችን ምታናግር የሆነች ከሃ* ዲውን ከሃ* ዲ ሙዕሚኑን ሙዕሚን ያለች ምትናገር።

10 ሰዎችን ሁሉ አንድ ቦታ ምትሰበስብ እሳት ትከሰታለች ሰዎች ከሷ የሸሹ አንድ ቦታ ይሰበሰባሉ። አላህም አንድት ምርጥ ንፋስ ይልካል በ ላኢላሀ ኢለሏህ ያመነውን ሁሉ ነፍስ ምትወስድ የሆነች የአላህ የሆነን ነገር ሁሉ ምትወስድ የሆነች!! ሙእሚኖች እንዳለ ያልቃሉ በአሽራሮች በክፉ ከሃዲዎች ላይ ቂያማ ትቆማለሽ። የዛኔ የዱንያ ነገር ያበቃለታል።

ጌታችን ሆይ የተውበት በርህ ሳይዘጋ በፊት እውነተኛ ተውባን ስጠን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group