Translation is not possible.

በመቶዎች የሚቆጠሩ በአሜሪካ የሚገኙ አይሁዶች እና ወዳጆቻቸው በአሁኑ ሰአት በኒዮወርክ በሚገኘው የነጻነት ሀውልት በፍልስጤም ላይ የሚፈጸመውን የግፍ ተግባር በመቃወም ተሰባሰበው ይገኛሉ ።

የኤስራኤል መንግስት በንጹኋን ፍልስጤማዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ ያወገዙት አይሁዶች በአንድ ወር ውስጥ ወደ 4,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ህጻናትን ጨምሮ ከ9,900 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። አሁን፣ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ጋዛ ውስጥ ያሉትን ሰፈሮች እና ዩኒቨርሲቲዎች ባብዛኛው በአሜሪካ በተሰራ ቦምቦች እያለቁ ነው ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል ።

አሁኑ ተኩስ እንዲቆም እንጠይቃለን ! ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል ።

ባለፈው ሳምንት የኒዮርክ ትልቁን ባቡር ጣቢያ ዘግተው የተቃወሙ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በኒዮወርክ የነጻነት ሀውልት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group