Translation is not possible.

የሳዑዲ ኢራን ጥምረት!

የሁለቱ የምዕራብ እስያ የከባድ ሚዛን ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በጋዛ ሰርጥ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ተወያይተዋል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂን እና የሳዑዲ አረቢያው አቻቸው ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን በስልክ ባደረጉት ውይይት የፍልስጤም ጉዳይ ላይ ያተኮረ የኢስላማዊ ሀገራት ትብብር ድርጅት (OIC) አስቸኳይ ጉባኤ ማካሄድን አስመልክቶ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በጋዛ ሰርጥ እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምትፈጽመውን የጦር ወንጀል ማስቆም እና በጦርነት ለተጎዱ ህዝቦች የማያቋርጥ ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል። እስራኤል በፍልስጤም ህዝብ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለመመክር የወቅቱ ሊቀመንበር ሳዑዲ አረቢያ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት በህዳር 12 በሪያድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ እንደሚካሄድ OIC ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Press Television

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group