Translation is not possible.

ሳዑዲን ያስጨፈረው ዲጄ፣

በጋዜጠኛ የኑስ ሙሃመድ የተፃፈ:-

በሳዕዲ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በዲጄዎች የታጀበ የጭፈራ ምሽት የዓለም ሙስሊሞችን አሳዝኗል። የአሳዛኝነቱ ምክንያት ምን እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሲሆን ብዙ ሰው የማያውቀውና ሙስሊሙን ጽኑ ድንጋጤ ውስጥ የከተተው ግን ነብዩ ሙሐመድ ሱዐወ ስለዚህ ዘመንና ስለአገራቸው የተናገሩትና ተፅፎ የተቀመጠው ነገር በዚህ በኛ ዘመን በመድረሱ ነው። ብዙዎች እንዳትረክስ ሲሳሱላት የነበረችው የነብዩ ሀገር በአሁኑ ንጉሷ የተነሳ ሌላ ማጥ ውስጥ እየገባች ነው ሲሉ የሚናገሩ ብዙ ናቸው።

እኔን የገረመኝና ይህን ጽሑፍ እንዳጋራችሁ ያደረገኝ ግን የሙዚቃ ኮንሰርቱ መከናወን ብቻ ሳይሆን ዲጄው ከጭፈራው በኋላ ለሚዲያ የሰጠው እጅግ በጣም አስገራሚና ለአንድ አማኝም አሳዛኝ የሆነ ቃለመጠይቅ ነው።

ጋዜጠኛዋ እንዴት ነበር ኮንሰርቱ? በሳዑዲ ታሪክ የመጀመሪያ እንደመሆኑ ምን ፈጠረብህ? የመፈቀዱ ምስጢርስ ምንን ያሳያል? አለችው፦

ዲጄው በከፍተኛ ደስታና መደነቅ ውስጥ ሆኖ መመለስ ጀመረ፦

"ይህ እጅግ በጣም ያስደነቀኝ ታሪክ ነው... በሳዑዲ አረቢያ ሴትና ወንድ አብረው ሲጨፍሩ ማዬት አስባችሁታል... እንዴት ደስ ይላል!? ገና ደሞ ወደፊት ብዙ ብዙ ነገር ይፈቅዳል ብለን እንጠብቃለን... ይህ መበረታታት ያለበት ጥሩ ጅምር ነው..."

ዲጄ ዴቪድ ጉታ "ገና ወደፊት ብዙ ነገር ይፈቀዳል.." ያለው ምን እንደሆነ መንገር አንባቢን ማድከም ነው። የሆነ ሆኖ ምዕራባውያን ትንሽ ቀዳዳ ሲያገኙ ከሰይጣን የባሰ መጥፎ ድርጊታቸውን ወደ አንዲት ሀገር እንዴት እንደሚያስገቡት የዚህን ሰው ንግግርና የፊት ሁኔታ አይቶ ብቻ መረዳት ይቻላል።

ዲጄው በዓለም ደረጃ ታዋቂ ነው ሌላ የትም ሀገር ዞሮ ያስጨፈረውና ራቂት ያስደነሰው ለሱ በቂ አይደለም ሳዑዲም ወደዚህ የአደባባይ መጠጥና ባህለ ወጥ ጭፈራ መቀላቀል አለባት ማለት ነው!? በአጋጣሚ በሸሪአ የምትተዳደር የሙስሊም ሀገር ሆና እንዲህ አሉ እንጂ የክርሥትያን ሀገርም ሆና በሳዑዲ ልክ ጥብቅ ህግ ቢኖራት ዲጄዎቹ ይሄን ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም ነበር።

ዓለማችን ለሙስሊምም ለክርሥትያኑም ከወትሮው በተለዬ ሁኔታ እየከፋች ነው። የአንዱ መኖር ለአንዱ አስፈላጊ የመሆኑን ያህል ያንዱ መርከስም ለሌላው መርከስ ነው። ሰሞነኛውን ነገር ሁሉ ላስተዋለና መንፈሳዊ እውቀት ላለው ሰው በምድራችን ላይ ምን እየመጣ እንደሆነ... ከዛስ ምን እንደሚከተል ለመተንበይ ግልጽ ነው።

ይህ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ቀደምት እንደታዩት እና በአደባባይ ወንጀላቸው የተነሳ ከምድረገጽ እንዲጠፉ የተበየነባቸው ህዝቦች ዓይነት 'ግልጽ ሀጢያት' የሚሰራበት ዘመን ነው።

ነገ ከሞት በኋላ ከፈጣሪ ፊት ቀርበን እንጠየቃለን ብለን ለምናምን የሰው ልጆች ሁሉ ፈጣሪ መልካም እሴቶቻችንን፣ ባህላችንንና እምነታችንን ይጠብቅልን።

👇

Send as a message
Share on my page
Share in the group