Translation is not possible.

#የቀጠለ....

ከላይ የተዘረዘሩትን በሟች ገንዘብ ላይ እሚንጠለጠሉ ሐቆችን በዝርዝር ስንመለከታቸው፦

1 ጅናዛውን ለቀብር ለማዘጋጀት የሚወጡ ወጪወች ስንል:-

የከፈን ዋጋ፣የሽቶ ዋጋ፣የጀናዛ አጣቢ ክፍያ፣የቀብር ቆፍሪ ክፍያና የመሳሰሉትን ያካትታል።

ይህ ሐቅ ከሁሉም ሐቆች አሳሳቢና ተቀዳሚ የሚሆነው የሟች ሐቅ ስለሆነ ነው።

2 ዕዳ ካለበት ለመክፈል የሚውል ገንዘብ :-በሁለት ከፍለን እንመለከተዋለን

2.1 የሟችን ንብረትና ገንዘብ በቀጥታ የሚመለከት የሌላ ስው ሐቅ

~>ይህ ሟች ለመበደር በማስያዦነት ያዋለው የሟች ንብረትን እና የመሳሰሉትን ያካትታል።

ይህ ሐቅ ከንብረቱ ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ ዕዳው ሳይከፈል ወራሾች ለማስያዣነት ባስያዘው ንብረት መጠቃቀም አይችሉም።

~>የስወች ሐቆች እነዚህ ዕዳዎች ሟች ከተወው ንብረት መከፈል ያለባቸው ሐቆች ሲሆኑ፦

ይህም ብድር(ማስያዣ ያልተያዘበት)፣የኪራይ ዕዳ፣የስው ደሞዝ፣ሟች ሆን ብሎ በስው ላይ ላደረስው ጉዳት የሚከፈል ካሳ፣ሟች ከስው ላይ ያጠፍው የስረቀው ንብረት ክፍያና የመሳስሉትን ያካትታል።

2.2 የሟችን ንብረት በቀጥታ የማይመለከቱ ዕዳወች ፦

የአላህ(ሱ.ወ) ሐቆች፦ ይህ እንደ ዘካ፣የሐጅ ገንዘብ (ሟች ሐጅ ማድረግ እየቻለ ሳያደርግ ከሞተ)፣ስደቀቱል ፈጥር፣ ከፍራ፣ለአላህ(ሱ.ወ) የገባው ስለትና የመሳስሉትን ያካትታል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group