Translation is not possible.

ሳዑዲ ግን…‼

===========

✍ አንዳንዶች በፈተና ጊዜ ይፈተናሉ‼

ምን አይነት አስተሳሰብ እንዳላቸው ባላውቅም ግራ ቀኝ ሳይመለከቱ ዝም ብለው ስሜታቸው ያመጣላቸውን እያወሩ ለአጉል ድምዳሜና ፍረጃ ይዳረጋሉ።

የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ሳዑዲ ዓረቢያን፣ መሪዎቿንና ዑለማዎቿን ሲኮንኑ ይስተዋላል። በተቃራኒው እንደ ኢራን ያሉ በአፍ የሚያወሩ ሃገራትን ይደግፋሉ።

በሰሞነኛው የጋዛ ጦርነት ሳዑዲ ላይ የተለመደውን መርዛማ አፋቸውን የሚከፍቱ እያየሁ ነው።

እስኪ አንድ ነጥብ ብቻ ላንሳ።

ሳዑዲ ለጋዛ በጦር መሳሪያ አግዛ ጦርነቱን በይፋ ብትቀላቀል ምንድን ነው የሚፈጠረው?

የሁለቱ ሐረሞች መቀመጫ መሆኗን አታስተውሉም? ጦርነት ትግጠም የምትሉት ደግሞ ሙስሊም ጠል ከሆነች ሃገር ጋር ነው። ከሑቲ ታጣቂዎችና መሰል ሙስሊም ነን ከሚሉ ቡድኖች ጋር ቢሆን ኖሮ፤ እንደ አርማኮ ያሉ ኢኮኖሚዋን ነክ የሆኑ ነገሮችንና የመንግስት ተቋማትን ለማጥቃት ይሞክራሉ እንጂ ደፍረው ሁለቱን ሐረሞች ኢላማ አያደርጉም።

እንደ እስራኤል አይነቱ መርዛማ ግን በተለይም ሊሸነፍ መሆኑን ካወቀና ተስፋ ከቆረጠ፤ ሁለቱ ሐረሞች የዓለም ሙስሊሞች የዓይን ብሌን መሆናቸውን አውቆ ኢላማ ሊያደርጋቸው ይችላል። ወይ ተፈትኖ የተዋጣለት የሚሳኤል መቃወሚያ የላቸው።

ባይሆን ሳዑዲ አሁንም ከሞላ ጎደል እያደረገች እንዳለው ፈለስጢማውያንንና ጂሃዲስቶቹን በስውር በገንዘብ መደገፍ፣ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት፣ በድብቅ የመሳሪያ ድጋፍ ማድረግ፣ ለተጎዱት ሕክምናና መሰል የእርዳታ ድጋፍ ማድረግ፣ በወራሪዋ ላይ ማዕቀብ መጣልና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ ማድረግ፣ ሪያድ አካባቢ የሚታዩ አንዳንድ ፈሳዶችን ማስቆም… አለባት።

ከርሷ ይልቅ እንደ ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ፣ ኢራን፣ ሊባኖስ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ኩዌት፣ ጆርዳን… ያሉ ሃገራት ግን በቀጥታ ጦርነቱን ቢሳተፉ ችግር አልነበረውም።

በነገራችን ላይ ሳዑዲ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለፈለስጢናዊያን ድጋፍ እያሰባሰበች ነው። 300 ሚሊዮን ሪያል ደርሳለች።

ንጉስ ሰልማንና ልጃቸው ደግሞ ከግል ገንዘባቸው 13 ቢሊዮም ዶላር ድጋፍ ሰጥተዋል። በኛ ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው። እስከዛሬም በየአመቱ ዘካ ታሰባስባለች። ሃገራትን ሞቢላይዝ ማድረግ፣ ጫና መፍጠር፣ ጥቃቶችን በጥብቅ ማውገዝ፣ ማስፈራራት… አይነት ሥራዎች በደንብ ቢገፋባቸው ይሻላል። ከሳዑዲ ከዚህ የበለጠ መጠበቅ ሞኝነት ነው የሚመስለኝ።

ባይሆን የዐረብ ሃገራት የሚያናድዱኝ፤ አሁን አሁን እየከዷት መጡ እንጂ የአሜሪካ አሽከር ሆነው ገንዘብ ሳያጡ ኒዩክሌር አለመታጠቃቸው። ሌሎች ለራሳቸው እየታጠቁ ሌላውን በስምምነት ሽፋን እየከለከሉ ያንን አምነው ከመቀበል ይልቅ ቢታጠቁ ማንም በቀላሉ አይደፍራቸውም ነበር። ያለብን የኢማን ድክመት እንዳለ ሆኖ!

ያም ሆነ ይህ ለፈለስጢናውያን ከመግለጫ ውጭ ምንም የፈየዳቸው ነገር የለም። እንዳውም አንዳንድ ሃገራት በሽምግልና ሽፋን የራሳቸውን ፖለቲካና ቅቡልነት እየሠሩባቸው እንጂ አልጠቀሟቸውም። ፈለስጢን አሁን ላይ የምትሻው የ"እናዝለን!" መግለጫ ሳይሆን ያለውን መሳሪያ ይዞ አብሯቸው የሚታገል ነው። ለእናዝናለንማ ኮሎምቢያና ቺሊ ይበቁናል።

ለማንኛውም አሁንም ቢሆን የእኛ ትችትና ሙገሳ በየሰዓቱ ለሚገደሉት የጋዛ ህፃናትና ሴቶች ስለማይጠቅም፤ ሁላችንም ከልብ ዱዓእ እናድርግላቸው። አላህ ዲሉን ያቀዳጃቸው።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group