Translation is not possible.

👉የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማህበር በጥቃቱ ከ12 በላይ ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።

👉በጋዛ የሚገኘው የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለፀው እስካሁን ከ9,200 በላይ ሰዎች በጋዛ ተገድለዋል። እስራኤል በበኩሏ ከ1,400 በላይ ሰዎች እንደተገደሉባት የገለጸች ሲሆን አብዛናው በኦክቶበር 7ቱ ድንገተኛ የሃማስ ጥቃት ወቅት የተገደሉ መሆናቸው ነው የተዘገበው፡፡

👉ባለፈው ሳምንት "ሀማስ ነጻ አዉጪ እንጂ አሸባሪ ድርጅት አይደለም" ሲሉ የተደመጡት የቱርክዬው ጠይብ ኤርዶጋን አሁን ደግሞ "የእስራኤሉ ናታንያሁ አሸባሪ ነው!" ሲሉ መወንጅላቸው ዳግም አነጋጋሪ አድርጓቸዋል፡፡

👉በአለም አቀፍ ደረጃ ከወትሮው በተለየ መልኩ በመላው አለም ፍልስጤማዊያንን የሚደግፍና በአስቸኳይ ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ!

Send as a message
Share on my page
Share in the group