Translation is not possible.

የእስራኤል የእብደት ጥግ‼

===================

✍ ተመድ ተብዬውና መሰል ጥርስ የሌላቸው አንበሶች ዝም ስላሏት፤ በጋዛ ከተማ ንጹሐን ላይ ሆስፒታልና የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ሳይቀር 24/7 እያዘነበችው ያለው ቦምብ አላረካት ብሎ ዛሬ የቅርስ ሚኒስተሯ እንዳሳወቀው ከሆነ ኒዩክሌር (አቶሚክ ቦምብ) ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በርግጥ ጠቅላይ ሚኒስተሯን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎች ይህንን የጓደኛቸውን ንግግር ለማውገዝ ሞክረዋል። ግን ምናልባትም ሚስጥር ለምን አወጣ ብለው ይሆናል እንጂ ውስጣቸው አይፈልገውም ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አሁን እየሄዱበት ባለው ጭፍጨፋ ካልረኩና የፈለጉትን ካላሳኩ አቶሚክ ቦምብ ላለመጠቀማቸው ዋስትና የለም።

በርግጥ እስካሁን ያዘነቡትም ቦምብ ሁለት አቶሚክ ቦምብ እንደሚገመት ተነግሯል።

ስለ አቶሚክ ቦምብ ለማታውቁ አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ኦገስት 6, 1945  በጃፓኗ ሒሮሽማ ከተማ ላይ፣ ከ3 ቀን በኋላ ደግሞ ናጋሳኪ ከተማ ላይ በጣለችው አቶሚክ ቦምብ እስከ 226,000 የሚጠጋ ህዝብ ነበር የጨረሰችው። እጅግ በጣም አውዳሚ መሳሪያ ነው።

እስራኤል በሰሜን ጋዛ አንድም መኖሪያ ቤት መኖር የለበትም ብላለች። የቀሩት ነዋሪዎችም ወደ ደቡብ ጋዛ ይሂዱ ብላለች። ግን መንገድ ላይና እዛው ደቡብ ጋዛ ላይም ማውደሟን ቀጥላለች።

ዓለም አሁንም ዝምታውን ቀጥሏል። ይህቺን እብድ ውሻ ማሰር አልቻለም።

አላህ በራሷ አቶሚክ ቦምብ ራሷን ያፈንዳትና ይገላግለን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group