ምርጥ ተውበት !
የ ታላቁ አሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ 🍃
ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ አናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ እያለ መጠጡን ገፍታ ደፋችባቸው የዛኔ ይህ አላህ በፋጢማ ተው እያለኝ ነው ብለው አሰቡ፣ ከአመት በኃላም ፋጢማ 3አመት ሞላት ከዛም ፋጢማ ሞተች። ከዛም ድጋሚ እንደበፊቱ መጠጣት መስከር ጀመሩ፣ ታዲያ አንድ ቀን ሸይጧን ወሰወሰኝ አሉ ዛሬ ሰክረኸው የማታውቀውን ስካር ነው የምትሰከረው አለኝ እሺ ብየ መጠጥ መጠጣት ጀመርኩ በጣም ሰከሬ ወደኩ አሉ ። ከዚያም በህልሜ ቂያማ የቆመ መሰለኝ ፀሀይቱ ጠቁራለች፣ ሰወ ሁሉ አላህ ፊት ተሰብስቧል፣ባህሩ ይነዳል የሰው ሁላ ስም ሲጠራ ቆየና ማሊክ ኢብኑ ዲናር ና ለሂሳብ ትፈለጋለህ ተባልኩ ከዛም ትልቅ ዘንዶ ማሳደድ ጀመረኝ እሱን ለመሸሽ ሰሮጥ አንድ ሽማግሌ አገኙሁ አግዘኝም አልኩት እኔ አቅሜ ደካማ ነው አለኝ ሰሮጥ የእሳት ጫፍ ላይ ደረስኩ፣ ዘንዶውን ፈርቼማ አሳት አልገባም ብየ ተመልሼ ሮጥኩ ድጋሚም ሽማግሌውን አገኙሁት አግዘኝም አልኩት አቅሜ ደካማ ነው እስቲ የምትድን ከሆነ ወደዛ ተራራ ሩጥ አለኝ። ከዚህም እየሮጥኩ እያለ ከተራራው ላይ ህፃኖች ፋጢማ አባትሽን ዘንዶ ሊበላው ነው ሲሉ ሰማሁ ። ለካ በ 3 አመቷ የሞተች ልጅ አለችኝ ብየ ወደ ፋጢማ ሮጥኩ ፋጢማም ዘንዶውን ገፍታ ጣለችው። እኔም ልጄ ሆይ እስቲ ያ ዘንዶ ምንድነው የሚያባረኝ አልኳት እሷም ያ መጥፎ ስራህ ነው አለችኝ እሺ ያ ሽማግሌውስ ያ ጥሩ ስራህ ነው አለችኝ ጥሩ ስራህ ደካማ ሰለሆነ ከመጥፎ ስራህ ሊያስጥልህ አልቻለም አለችኝ። ከዛም 1የቁርአን አያ ቀራችልኝ።
"እነዛ ምእመናን ልባቸው ለአላህ ግሳፄ የሚፈራበት ግዜ አልደረሰምን?" የሚለውን አነበበችልኝ ። ልክ አኔም ከእንቅልፌ አዎ ግዜው ደርሷል አያልኩ እያለቀስኩ ተነሳሁ ሻወር ወሰድኩ ሱብሂ ወደ መስጂድም ሄድኩ። መስጂድም ኢማሙ ይህንኑ አያ እየቀሩት ነበር አልቅሼ ተመለስኩ ይሉናል ታላቁ ኢማም።
እኝህ ሰው ህዝቡን የሚያስተምሩ ታላቅ ኢማም ሆኑ። ሁሌም መስጂድ አንተ አላህን ያመፅክ ባሪያ ሆይ ወደ ጌታህ ተመለስ ይሉ ነበር።
copy