Translation is not possible.

ዉበትሽ ለማነዉ?????

   ስለገረመኝ ነዉ የአኼራ እህቴ

   መልስን በመፈለግ ጥያቄ ማሳቴ

   ከቁረአን ከሀድስ መረጃሽን ስጭኝ

    መዋብሽ ማጌጥሽ ለማነዉ ንገሪኝ

ከቤት ስትወጭ መኳኳል ሽቶ መነስነሱ

ለህዝቡ ነዉ እዴ ለጅን ለኢንሱ

አባያ ቀሚሱን ፋሽን ተቀምሮ

ወገብ ከደረትሽ የፊጥኝ ታስሮ

ቅርፁ ጎልቶ ወጣ መሰለ ማሰሮ

ይህ ሁሉ ጋጋታ ማነን ለመማርክ

ባልሽን ነዉ ህዝቡን ማንን ለማበርከክ

የት ጠፍ ተቅዋሽ ሀይእን ምን በላዉ

ለባል ሳትዋቢ ለህዝቡ ምንድን ነዉ

መደሰት ያለበት መማርክ ያለበት

የመልክ ቁጅና ባልሽ ነዉ ባለቤት

መዋብሽ ማጌጥሽ ከሆነ ለህዝቡ

እሱን ችላ ብለሽ ከወጣሽ ከልቡ

ትዳሩም ይፈርሳል ቤቱም ይበተናል

ነገም በአኼራ ከችሎት ይቀርባል

ሳይፈረድ ንቂ ፍቅራችሁ ይታደስ

መዋብ ለባል ሁኖ ኒቃቡ ይለበስ

እኔ ልምረጥልሽ ሸሪአን ያሟላ

መሆንን ከፈለግሽ የድንሽ ከለላ,,

     

Send as a message
Share on my page
Share in the group