የእስራኤል ጦርነት ግብ ምንድን ነው?
ማህበራዊ ተቋማቶች እና የልማት መሰረተ ልማቶች በማህበረሰቡ ህይወት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እየ ሆነ ያለው የእስራኤል ፍላጎት ሃማስን ለማጥፋት ብቻ እንዳልሆነ ያሳያል። ይህም ማለት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የመብራትና የውሃ ምንጮችን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ የንግድ ተቋማትን፣ ቤቶችን እና ንፁህ ፍልስጤማውያንን በጅምላ እንዲገደሉ እያደረጉ ያሉት ህዝቡን ከመሬቱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማንሳት በማሰብ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ግን እስላማዊ ነን የሚሉ ሀገራት መንግስታት በጅምላ እየተገደሉ በረሃብና በጦርነት እሳት እየተቃጠለ ያለውን ህዝብ በዝምታ ማየታቸው ነው።
አላህ ሆይ ይህ በባሪያዎችህ ላይ እየደርሰ ያለውን ከመጠን ያለፈ ጭቆና ይበቃል በላቸው ። ስፍር ቁጥር በ ሌለዉ ሰራዊቶችህ አግዛቸው።
በህይወት እያለን ድላቸውን አሳየን ያ ጀባር!!! ያ ቃህሀር!!!