Translation is not possible.

አውሮፓ ከኤስያ ጋር በባህር የሚገናኙት በግብፁ የስዊዝ ካናል ወይም ቦይ አማካኝነት ነው። በዚህም ግብፅ በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላር ከቀረጥ ታገኛለች።

አሁን ደግሞ እስራኤል ስዊዝን የሚተካ ቤንጎሪዮን የተባለ ካናል የመስራት ዕቅድ አላት። ይህ ካናል ደግሞ መሰራት የሚችለው በጋዛ በኩል እስከ አቀባህ ነው። እናም እስራኤል ለዚህ ካናል መሳካት ጋዛዎችን ወደ ሲና በረሃ ማባረር ትፈልጋለች።

ቦዩ ከጋዛ ባሻገር ይቆፈር ከተባለ ደግሞ ጋዛ ጂኦግራፊካሊ ከእስራኤል የተገነጠለ ስለሚሆን ከቁጥጥሯ እንዳይወጣ ትፈራለች።

ግብፅ ደግሞ ይህ ካናል ከተሰራ አውሮፓውያን እሷን በመተው በእስራኤል በኩል ስለሚሻገሩና ካናሏ ከግመል ማጠጫ ባለፈ ጥቅም ስለማይኖረው ጋዛወች በሲና መስፈራቸውን ፈፅሞ አትቀበልም።

ከዚህ በተጨማሪ በሲና በረሃ በርካታ ኢስላማዊ ቡድኖች ስላሉ ይተባበሩብኛል የሚል ፍራቻም አለ።

እናም የሰሞኑ ጦርነት እስራኤሎችና ምዕራባውያን ከሐማስ ባለፈ ዘላቂ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሞክሩበት ይመስላል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group