Translation is not possible.

አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት

ልብ አንጠልጣይ ታሪክ......!!

⏠⏠

ክፍል ⓷

⏡⏡

⏃እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው በአላህ ስም ጽሁፌን ጀምራለሁ፡፡ አንች ወጣት ሆይ ጌታችን አላህ ባሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያምጸው ወዲያዉኑ አይቀጣውም፡፡ ይልቁንም ታግሶ ያልፈዋል፡፡ ሌላንም ጥፋት ቢጨምር አያጋልጠውም፡፡ ይልቁንም ይሰትረዋል፡

⎇ ነገር ግን ወንጀሎችን በንቀት አይን ሲመለከትና እንደተራ ነገር ሲቆጥር፣ ሃጢያቶችን በአደባባይ በግልጽ ሲፈጽም እንድሁም በጥፋቱ ላይ ሲዘወትር አሸናፊና ሃይሉ ጌታ በባሪያው ላይ በጣም ከባድን ቁጣ ነው የሚቆጣው፡፡

≾ በእንደዚህ አይነት ሰው ላይ ጌታችን የሚኖረው ቁጣ ሰማያት የሚጠቡበት፣ መሬት የምትጨነቅበት፣ ተራራዎች፣ ዛፎችና እንስሣቶች ሁሉ በጣም የሚርበተበቱበት አይነት ቁጣ ነው ፡፡

≼ ታዲያ ይሄን አይነቱንየጌታችንን ቁጣ ማንኛችን ነን የምንችለው? በየትኛውስ አቅማችን ነው የምንቋቋመው? ስለዚህ ወጣቷ ሆይ ሰማይ እንደ ዘይት የምትቀልጥበትን፣ ተራራዎች እንደተነደፈ ሱፍና ጥጥ የሚበታተኑበትን፣ ከሀዲዎች በጥፋታቸው በመጸጸትና በክስተቱ በመደናገጥ በጉልበታቸው የሚንበረከኩበትን፣ እናቶች በእቅፋቸው ሆኖ የሚጠባውን ልጃቸውን የሚዘነጉበትን እለት እንድትጠነቀቂው ነው የምመክርሽ፡፡

≾ በተጨማሪም ልታውቂው የሚገባ ነገር ቢኖር እኔ አይደለም አንችን ማስተካከል ራሴንም መቆጣጣር እና ማስተካከል የተሳነኝ ደካማ ፍጡር ነኝ፡፡ ስለዚህ በእሱ እጠቀማለሁ ብለሽ አስበሽ ከሆነ ይሄን አመለካከትሽን አስተካክይው፡፡

≲ ምናልባት ቀልብሽ እኔ ላይ ያረፈው በበሽታ ምክንያት ከሆነ ደግሞ የተሰበረን የሚጠግን፣ የቆሰለን የሚያክም፣ የታመመን የሚያሽር አስተማማኝ ሃኪም ጠቁምሻለሁ፡፡ እሱም የአለማቱ ጌታ አላህ ነው፡፡ በቀና ልቦናና በእውነተኛ ቀልብ የምትፈልጊውን ሁሉ ጠይቂው፡፡

≃ እሱ የጠያቂዎችን ጥያቄና የለማኞችን ልመና ከንቱ የሚያስቀር ጌታ ስላልሆነ ያሰብሽውን ያሳካልሻል፡፡ የሚጠቅምሽን ሁሉ ይሰጥሻል፡፡ እኔግን አሁን ስላንቺ የማስብበት ወቅት ላይ አይደለሁም፡፡ እኔ የሚያስጨንቀኝ

{ وَأَنذِرۡهُمۡ یَوۡمَ ٱلۡـَٔازِفَةِ إِذِ ٱلۡقُلُوبُ لَدَى ٱلۡحَنَاجِرِ كَـٰظِمِینَۚ مَا لِلظَّـٰلِمِینَ مِنۡ حَمِیمࣲ وَلَا شَفِیعࣲ یُطَاعُ }{ یَعۡلَمُ خَاۤىِٕنَةَ ٱلۡأَعۡیُنِ وَمَا تُخۡفِی ٱلصُّدُورُ }

⊰ ልቦች በጭንቀት ከመሞላታቸው የተነሳ ላንቃ የሚደርሱበትን ቅርቢቷን የትንሳኤ ቀን አስጠንቅቃቸው፤ በእለቱ በደለኞች ምንም አይነት እገዛን የሚሰጣቸው ወዳጅ እንድሁም ተቀባይነትን የሚያገኝ አማላጅ የላቸውም፤ ጌታችንም የአይኖችን ክህደት (ሽወዳ) እንድሁም ልቦች የሚደብቁትንም ሃሳብ ሁሉ ያውቃል” ” ጋፊር 18_19 የሚለው የጌታዬ ቃል ነው፡፡

≋ እኔ የሚያስጨንቀኝ ይሄንን እለት በምን መልኩ እንደማመለጥ ማሰብ ነው ይላል ለወጣቷ የተጻፈላት ደብዳቤ፡፡

✍️ይቀጥላል.......

ሰምተው አብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን

ፎሎ ሼር ላይክ ማድረግ ሳይረሳ

Send as a message
Share on my page
Share in the group