Translation is not possible.

የሴቶች መበላሽት ዋና ሰበቡ የወንዶች መዘናጋት ነው

አባት ልጁን በሸሪዓዊ አስተዳደግ ቢያሳድጋት

ባልም ሚስቱን በሸሪአዊ አያያዝ ቢይዛት ኖሮ ብዙ ሴቶች ባልተበላሹ ነበር

ውዷ እህቴ ውድ ትሆኝ ዘንድ ቁጥብ ሁኝ

ሁሉም የሚዘግንሽ ቆሎ አትሁኝ

ያየሽውን ሁሉ አታውሪ ቆፍጠን በይ በርሽን ላገኘሽው ሰው አትክፈች

ክብርሽ ጠብቂ በቃ መገኘት የሌለብሽ ቦታ አትገኝ

ሚስትርሽን እንጅ እውቀትሽን አትደብቂ ያወቅሽውን አሳውቂ ስሜትሽን አሸንፊ

ጀግና ሴት ማለት የወጣትነት ግዜዋን ለጌታዋ የሰጠች ነች

በሸሪዓ ልጓም የምትተዳደር

ወጣትነትሽን ተጠቀሚበት አላህ ለፈጠረሽ አላማ ኑሪ

ጓደኛሽን ምረጭ

በዙሪያሽ ያሉ ጓደኞችሽ ላንች እንደ መሰላል ናቸው

ጥሩ ሆነው ወደላይ ከፍ ያረጉሻል

አልያም መጥፎ ሆነው ወደታች ያወርዱሻል።

እናማ ውዷ ውሎሽን ምረጭ ቆም ብለሽ አስቢ

ታዋቂ ሳይሆን አዋቂ ለመሆን ጣሪ

በምንማራቸው ኪታቦች ስፋት ክብደትና ትልቅነት ብቻ ትልቆች ወይም ከባዶች አንሆንም። ትልቆች መሆን የምንችለው የተማርነውን ተግባራዊ ለማድረግ ስንችል ነው።

የተማርነውን ዐቂዳ፣ኢባዳ እና አኽላቅ ተግባራዊ ማድረግ ስንችል

በሁለቱም አለም ስኬታማ እንሆናለን።

ውዷ አላህ የተግባር ሰዎች ያድርገን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group