Translation is not possible.

"በእስራኤል ላይ ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛ ላይ ናቸው" የሂዝቦላህ መሪ

ሲጠበቅ የነበረው የነስረላህ ንግግር በትንሹ

የሂዝቦላህ ዋና ጸሃፊ ሀሰን ናስራላህ በእስራኤል ላይ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ እንዳሉ በመግለጽ የጽዮናውያን አገዛዝ በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስበዋል። ነስራላህ ተላንት በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግር ላይ ሂዝቦላህ ለሁሉም አማራጮች ዝግጁ መሆኑን ደጋግሞ ተናግሯል።

የሂዝቦላህ ዋና አዛዥ እንዳሉት ቀጠናዊ ጦርነትን ለመከላከል የሚፈልግ ሁሉ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት በፍጥነት ማስቆም አለበት። በሊባኖስ ግንባር ላይ ጦርነቱ ወደ “ሰፊ ዉጊያ” የመቀየር ሰፊ እድል እንዳለ አስጠንቅቋል።

“እናንተ፣ አሜሪካውያን፣ በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም ትችላላችሁ፣ ምክንያቱም የእናንተ ወረራ ነው። ቀጠናዊ ጦርነትን ለመከላከል የሚፈልግ ሁሉ እና እኔም ለአሜሪካውያን የምናገረው በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በፍጥነት ማቆም አለባችሁ የሚለውን ነው።

“እናንተ፣ አሜሪካውያን፣ በአካባቢው ጦርነት ከተነሳ፣ መርከቦቻችሁ ምንም እንደማይጠቅሙ፣ ከአየር ላይ መዋጋትም ምንም እንደማይጠቅም እና ዋጋ የምትከፍሉት ፍላጎቶቻችሁን፣ ወታደሮቻችሁን እና የጦር መርከቦቻችሁን በማጣት” መሆኑን ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ። ሲል ተናግሯል።

ነስራላህ ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው የምታሰማራውን የጦር መርከቦችን በተመለከተ ሂዝቦላህ አያስፈራውም ብለዋል። መሪው ሂዝቦላህ በሜዲትራንያን ባህር ላይ በሚገኙ የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን የተናገሩ ሲሆን “በቅንነት እነግራችኋለሁ፣ የምታስፈራሩብንን ለመርከቦቻችሁ በደንብ አዘጋጅተናል” ብሏል።

የፍልስጤም ሙጃሂዶች በእስራኤል ወራሪ ሃይሎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በከፈቱበት ማግስት የሊባኖስ ተቃውሞ ሀይሎች ከእስራኤል ጋር ጦርነት ዉስጥ የገባ ሲሆን ነስራላህ በሊባኖስ ድንበር ላይ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በየቀኑ የሚካሄደው የተኩስ ልውውጥ መጠነኛ ቢመስልም በጣም አስፈላጊ እና ከ1948 ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብለዋል።

ናስራላህ ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ጉልህ እና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ያሉ ሲሆን የሂዝቦላህ አለቃ እስካሁን 57 የሂዝቦላህ ተዋጊዎች ሰማዕት ሆነዋል ብለዋል። ይህንን የተናገሩት እስራኤላውያን በጋዛ ሰርጥ ላይ ያደረሱት ጥቃት እ.ኤ.አ ኦክቶበር 7 ከጀመረ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ነው።

የእስራኤል አገዛዝ በተከበበችው የጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ እየፈፀመው ላለው ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ “ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናት” በማለት እስራኤልን እንደ አንድ መጠቀሚያ ብቻ ናት ሲሉ ጠርተዋል። "በጋዛ እና በህዝቦቿ ላይ ለቀጠለው ጦርነት አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናት፣ እና እስራኤል በቀላሉ የግድያ መሳሪያ ነች" ሲል ናስራላ ግጭቱን "ወሳኝ" በማለት ገልፆታል።

"ቀጠናዊ ጦርነትን ለመከላከል የሚፈልግ በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በፍጥነት ማቆም አለበት" ይህ ለአሜሪካውያን ነው ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ "የተኩስ ማቆም እና ጥቃቱን ማብቃት እንቅፋት ሆናለች" ብለዋል.

“የአል-አቅሳ ማዕበል 100% የፍልስጤማዊያን ነበር” ነስረላህ ኦፕሬሽን አል-አቅሳ ማዕበል ሙሉ በሙሉ የተካሄደው በፍልስጤም ሙጃሂዶች መሆኑን ተናግሯል።"ታላቁ የአል-አቅሳ ማዕበል ኦፕሬሽን 100 በመቶ ፍልስጤም ተወስኖ ተግባራዊ ሆኗል" ብለዋል. የሊባኖስ የሂዝቦላህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሪ አክለውም “ፍፁም ሚስጥራዊነቱ የአል-አቅሳ ማዕበል ስኬትን ያረጋገጠ ነው።

"የሃማስ የጥቅምት 7 የጥቃት እቅድ መደበቅ አላስቸገረንም" ሲል ተናግሯል። “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፍልስጤም ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ነበር፣ በተለይም በዚህ ጽንፈኛ፣ ሞኝ፣ ደደብ እና አረመኔ [የእስራኤል] አገዛዝ ላይ የተወሰደ ትክክለኛ እርምጃ ነው” ብሏል።

“ኦፕሬሽን አል-አቅሳ ማዕበል [በእስራኤል] ውስጥ ምድርን ያንቀጠቀጠ ነው። "ስትራቴጂካዊ እና ነባራዊ ተጽእኖዎች አሉት እናም ውጤቱን በ [እስራኤል] የወደፊት ጉዞ ላይ እናየዋለን ያሉ ሲሆን። በጋዛ እየሆነ ያለው ነገር የእስራኤልን ሞኝነት እና አለመቻል ያሳያል ምክንያቱም እያደረገች ያለችው ህጻናትን እና ሴቶችን መግደል ነው ብሏል።

"እስራኤል ምንም አይነት ወታደራዊ ስኬት አላስመዘገበችም" የሂዝቦላህ መሪ እስራኤልን “ደካማ” በማለት ለአንድ ወር ሙሉ አንድም ወታደራዊ ስኬት ማስመዝገብ እንዳልቻለች ተናግሯል። ነስራላህ በጋዛ እና በተያዘው ዌስት ባንክ ለተገደሉት ቤተሰቦች "ሀዘን እና እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት" አስተላልፈዋል። “ይህ መስዋዕትነት በሰዎች፣ በሥነ ምግባር እና በሃይማኖት ደረጃ ያለ ትልቅ ክብር ነው። እሱ በጣም ግልፅ ሐቅ እና እጅግ የላቀ ነው ፣ ”ሲል ተናግሯል ።

የሂዝቦላህ አለቃ “የእኛ እውነተኛ ጥንካሬ ያለን ጽኑ እምነት፣ ያልተናወጠ ጥንካሬ፣ ያለን ታማኝነትእና ለትግሉ ባለው ቁርጠኝነት ላይ ነው” ብለዋል። ነስራላህ ንግግሩን የጀመረው የሂዝቦላህን “የወደቁ ሰማዕታት” እና ከእስራኤል ጋር የሚዋጉትን ሌሎች ተቃዋሚ ቡድኖችን እንዲሁም የተገደሉትን ሲቪሎች በማወደስ ነው። "በሊባኖስ ለሞቱት ቤተሰቦች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ እጀምራለሁ፤ በተመሳሳይም ወዳጅ ዘመዶቻችሁ የሰማዕትነት ክብር ስላገኙ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን" ብሏል።

“በዚህ ቅዱስ ጦርነት ውስጥ ለተሳተፉት የኢራቅ የየመን እና የሊባኖስ ጀግኖች ሰላምታ መስጠት አለብን” ብለዋል ፡፡"በዋሽንግተን እና ለንደን ውስጥ ወንበዴውን አካል እና ደጋፊዎቹን የሚያናውጥ ትልቅ ሰልፍ መሆን ነበረበት እና ይህ የተባረከ ተግባር የተከናወነው በዚህ ጊዜ ነው" የሂዝቦላህ ባለስልጣን የእንቅስቃሴው ምላሽ "የማያሻማ" መሆኑን ጎላ አድርጎ ገልጿል, የቡድኑን ነፃነት እና ለራሱ አጀንዳ የማይናወጥ ቁርጠኝነትን አጽንኦት ሰጥቷል.

አገዛዙ በጋዛ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ካጠናከረ እና የውጭ ወታደራዊ ሃይሎች ጣልቃ ከገቡ የፍልስጤምን መንግስት በጦርነቱ ለማገዝ የፍልስጤም ተቃዋሚ ሃይሎችን ሃማስ እና አጋሮቹን በእስራኤል ላይ በሚደረገው ውጊያ በይፋ እነደሚገባ ሂዝቦላ አስጠንቅቋል።

Please share https://ummalife.com/post/225701

✍Mohammed Y. via Press Television

#palestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group