🔶የወሊድ መከላከያ(contraceptive) መጠቀም?🔶
👉ጠያቂው ይላል፦ባልና ሚስት የወሊድ መከላከያ(contraceptive)ለመጠቀም ቢስማሙ ይህም ሚስትየው ስለታመመች ሳይሆን አራት ልጆች ብቻ እንዲኖራቸው በመስማማታቸው ነው።ህልማቸውም ተሳክቶ ከዚያ በኋላ ሚስት ከባሏ በመስማማት መከላከያውን ተጠቀመች።የዚህ ነገር ፍርዱ ምንድነው?እናም ባል ሳይስማማ ብትጠቀመውስ ፍርዱ ምንድነው?በዚህ ላይ ወንጀል እና ሸሪዓን መፃረር አለበትን?
👉ሸይኽ ኢብኑ ዑثይሚን(رحمه الله) ሚስት ያለ ባሏ ፈቃድ የወሊድ መከላከያ መውሰዷ በሷ ላይ ሀራም ነው።ምክንያቱም ለባሏም በልጆቹ ጉዳይ ሐቅ አለውና።ከሰዎች ብዙዎቹ(በዋነኝነት)ሚዘወጁት ልጆችን ፍለጋ እንጂ ለሌላ አይደለም።መከላከያውን በባሏ ፈቃድ መውሰዷን በተመለከተ እዚያ ላይ ሀጃ ያለባት ከሆነ-እርግዝናው ከተከታተለ ይህችን ሴት ሚያደክማትና ሚከብዳት ከሆነ በተለይም ቶሎ ቶሎ ከሚያረግዙት ከሆነች የዛኔ በባሏ ፈቃድ መጠቀሟ ችግር የለበትም።ነገር ግን እዛላይ ሚጣራ ነገርና(እንድትጠቀም በቂ ምክንያት)እና ሀጃ ከሌለ ልትጠቀም አይገባም።ምክንያቱም ይህ ነገር ሸሪዓችን ልጆችን ከማብዛት አንፃር ተፈላጊ የሆነውን ነገር ስለሚጋፋ ነው።ልጆችን ማብዛት ተፈላጊ እና የተጠበቀ ጉዳይም ጭምር ነው-ከኡማው ልቅእና ነው።አላህ(سبحانه وتعالى)በርግጥም በኢስራኢል ልጆች ላይ እንዲህ በማለት ተመፃድቋል(በፀጋው አስታውሷቸዋል)"ከነገድም የበዛችሁ አደረግናችሁ"(አል-ዒስራእ:6)እንዲሁም ነብዪሏሂ ሹዐይብም(عليه السلام)ህዝቦቹን እንዲህ በማለት አስታውሷቸዋል"ጥቂጦችም በነበራችሁና በበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ"(አል-አዕራፍ:86)ነብያችንም(عليه الصلاة والسلام)የቂያም እለት በኡማቸው ብዛት በነብያቶች ይፎክሩባቸዋል(ይፎካከሩባቸዋል)።
ይህ ሰው(ባል)እና ሚስት አራት ልጆች ብቻ እንጂ ከዚያ በላይ የማይፈልጉ ሆነው የመስማማታቸው ሁኔታ ከነሱ የሆነ ስህተት ነው።እነዚህ አራቶቹም ልጆች ወይም ከፊሎቹ ሊሞቱ ይችላሉ።ሲቀጥል ማነው የልጆች ብዛት አራት ነው ያለው?።በል እንደውም ልጆች በበዙ ቁጥር በላጭ እና ለሰው ልጅ ልቅእና ነው ሚሆነው።አላህ(سبحانه وتعالى)በነዚህ ልጆች(ስበብ) መልካም ነገርን:በረከትን:እውቀትን እና በአላህ መንገድ መታገልን ሊያደርግ ይከጀላልና ከነሱ(ባልና ሚስት)ይህን(የልጆች ቁጥርን መገደብ)መተግበር አስፈላጊ አይደለም።
📖(ኑሩን ዐላ ኧድ-ደርብ)
📗ማጠቃለያ
🔹ድህነትን ፈርቶ የወሊድ መከላከያን መጠቀም አይቻልም-ስለሁሉም ሪዝቅ አላህ ቃል ገብቷልና።
🔹ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በመደራረቡ ጉዳት ሚያመጣ ከሆነ እና በልጆቹም እድገት እና እንክብካቤ በማድረጉ ሂደት ችግር(non economical)ሚገጥም ከሆነ ብትጠቀም ችግር የለውም
🔹ምትጠቀመው መከላከያ እስከመጨረሻው መውለድን ሚያግድ መሆን የለበትም።ይልቁንም በሀጃዋ ያህል መሆን አለበት።
🔹በሀጃዋ ያህል ከሆነ ክኒንም(oral contraceptive) ይሁን IUD ወይም ሌላ አይነት መጠቀም ትችላለች።( ጎንዮሽ ጉዳትን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደተጠበቀ ይሆናል።)