Translation is not possible.

አላህ ዘንድ የቀለለ ሰው የሰዎች ውዳሴ አይጠቅመውም

~

በሰው እጅ እሳትም ሆነ ጀነት የለም። ስለሆነም የሰዎች ጭብጨባና አድናቆት ግብ ሊሆን አይገባም። አላህ ከፍ ያደረገውን የምቀኞች ክፋት አያወርደውም። አላህ ዝቅ ያደረገውን ጭብጨባና ከንቱ ውዳሴ አይሰቅለውም። ስለሆነም የሰዎች ውግዘት ጭንቀትህ፣ ውዳሴያቸው ደግሞ መሻትህ አይሁን። ይልቁንም ለትእዛዙ በማደር ጌታህ ዘንድ ከፍ ለማለት ጣር። ኢማሙል አውዛዒይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦

ﺇﻥّ من الناس مَن يُحِبُّ الثّناء عليه، ﻭﻣﺎ يُساوي عند الله جناح بعوضة

"ከሰዎች ውስጥ መወደስን የሚወድ አለ። አላህ ዘንድ ግን የትንኝ ክንፍ አያክልም።" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 8/255]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

IbnuMunewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group