Translation is not possible.

ሁሉም ልጆቿ በወራሪዋ ጦር ሲገደሉባት እርሷ ግን ቆስላም ቢሆን ተረፈች። ህመሟን ዋጥ አድርጋ "ለኢየሩሳሌምን ይሁኑ ፊዳ! ልጆቼ ስለቁድስ ተሰው" እያለች ሸሃዳን ትደጋግማለች። ኸንሳእን አስታወሰችን።

ከቃዲሲያ ዘመቻ ከአንድ ቀን በፊት አራት ወንዶች ልጆቿን የሰበሰበችው ጀግና "ጦርነት ቀሚሷን ወደላይ ስትሸመልል ካያችሁ ወደፊት በመቅደም የጠላትን የጦር መጋብርት ግጠሙ፡፡ የጀግንነት ቤታችሁን በክብርና በአሸናፊነት ሞገስ ታገኛላችሁ” ያለችው ድንቅ ሴት ታወሰችኝ፡፡

የውጊያ ሚዛኑ ወደ ሙስሊሞች አጋድሎ ፋርሶች ትልቅ ኪሳራን ከሰሩ፡፡ አስር ሺህ ተገደለባቸው፡፡ ከሙስሊሞች ሰልፍ አንድ ሺህ ሲሰው ሸሂድ ከሆኑት ውስጥ አራቱ የኸንሣእ ልጆች ይገኙበት ነበር፡፡ ዜናው በደረሳት ጊዜ እንዲህ አለች:-

"በነሱ መገደል ያከበርከኝ ጌታ ምስጋናዬ ይድረስህ አልሀምዱሊላህ በነሱ ሸፈዓን እንደማገኝም ከጌታዬ እከጅላለሁ" አለች፡፡

ኸንሳእ በጃሂሊያ ዘመን የዘፈን ግጥሞችን በመግጠም ትታወቅ ነበር፡፡ እነሆ ዛሬ አራት ወንድ ልጆቿ በአላህ መንገድ ተዋግተው መስዋዕትነትን እንዲቀበሉ መከረቻቸው፡፡ ኢማን የሚያስገኘው ተአምራዊ ለውጥ ይሏል እንዲህ ነው።

#mahi mahisho

ቴሌግራም

👇👇👇

t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

ኡማ ላይፍ

👇👇👇

https://ummalife.com/mahimahisho

9 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group