Translation is not possible.

ፊትን በአማኢም መሸፈን የጀግንነት ምልክት ነው። ለዘመናት የተሻገረ የሙስሊም ሙጃሂዶች ልብስ

አብዛኞቹ ሰሐቦች ወደ ጦር ሜዳ ሲገቡ ይጨነበላሉ። ዙበይር በቢጫ አቡ ሐምዛና ሚህጀንም በቀይ ጥምጥም ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር። ማነው አቡ ሚህጀን?!

እርሱ የአላህንና የነቢን ጠላት በማሸበር ወደር ያልተገኘለት ጀግና። ወደ ጦር ሜዳ ሲገባ ጭንቅላቱ ላይ የሚጠመጥማት ቀይ አማይማን የተመለከተ ከሐዲ በፍርሐት ይርዳል። አንድ መሰረታዊ ችግር ግን ነበረበት። ሁሌም ይጠጣል። ጭንብስ ብሎ ይሰክራል። የአላህን ህግ በተደጋጋሚ እየጣሰ አስቸግሯልና በአደባባይ ብዙ ጊዜ ተገርፏል። ከዚህ ተግባሩ ባለመላቀቁ በእግረ ሙቅ ተጠፍሮ በግዞት ወደ እስር ቤት ተወርውሯል።

ዕለቱ የቃዲሲያ ዘመቻ ወቅት ነበር። አቡ ሚህጀን የታሰረው ጦርነቱ ከሚካሄድበት ቦታ ብዙም አይርቅም። የፈረሶችን ማሽካካት የሰይፍ ግጭቶችና የተክቢራ ድምፆችን ሲሰማ መታሰሩን አምርሮ ጠላ። ከተጋጋለው ጦር ገብቶ የአላህን ጠላቶች አንገት በሠይፍ መሸልቀቅን በእጅጉ ናፈቀ። ከአይኖቹ እንባን እያረገፈ ውስጡ ክፉኛ ተረበሽ። የጂሃድ ናፍቆት እንደነበልባል እያንገበገበ አላስችል ቢለው የታሰረበትን ክፍል በር ደብድቦ ለጦር መሪው ሚስት መልዕክትን ላከ። እንዲህም አላት "ካቴናዬ ተፈቶ የጦር መሳሪያና ፈረስ አዘጋጅተሽ የናፈኩትን ጂሃድ እንድካፈል አድርጊኝ። እባክሽ እፋለም ዘንድ እርጂኝ። በህይወት ከተረፍኩ ራሴ መጥቼ የእስር ቤቱን በር በላዬ ላይ እከረችማለሁ" አላት።

ንግግሩን ስትሰማ አዘነች የመጣው ይምጣ ብላ በራሷ ወሰነች። ፈረስና ሠይፍ ሰጥታ ለቀቀችው። አቡ ሚህጀን ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ከጦር ሜዳው መሐል ሰፈረ። የአላህ ጠላቶች የበላይነትን ለመቆጣጠር ቀርበዋል። የሙስሊሙ ጦር ተዳክሟል። በዚህ ቅፅበት አቡ ሚህጀን ከመሐላቸው ተከሰተ። አንዱን በአንዱ ላይ አነባበረ። ድል ወደ ሙስሊሞች ማዘንበል ጀመረ። አቡ ሚህጀን የአላህንና የሙስሊሙን ጠላቶች አረገፋቸው። ከፊቱ የቀረበን የጠላት ጦር አንገቱን ቀንጥሶ መሬት ላይ እየጣለ፣ ያገኘውን እየገነዳደሰ ወደመሐል ገሰገሰ።

የጦር መሪው ሰዕድ የዚህን ተዋጊ ገድል እየተመለከተ ነው። እንዲህ በፅናት የአላህን ጠላቶች አመድ የሚያደርገው ማን ነው ሲል ይጠይቃል። የሚያውቀው ሰው ጠፋ። አቡ ሚህጀን ነው እንዳልል እሱን አስሬዋለሁ ይላል።

ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል አድራጊነት ሲጠናቀቅ ወደ እስር ቤቱ ተመለሰ። እነዛን በጦርነት የደከሙ እግሮቹንና እጆቹን በካቴና ጠፍሮ አሰራቸው። ሰዕድ ወደ ቤት ሲመለስ ሚስቱ ውሎውን ጠየቀችው።

ሰዕድም የሽንፈት ማቅ ልንከናነብ በተቃረብንበት ወቅት አላህ አንድ ልዩ ተዋጊ ላከልን። ያ የመነመነ የድል ተስፋ ተቀልብሶ ለማሸነፍ በቃን። አቡ ሚህጀንን አስሬው ባልሄድ ኖሮ ያ ጀግና ተፋላሚ እሱ ነው ብዬ እጠረጥር ነበር። የጦር ስልቱ የእሱን ይመስላል በማለት ተናገረ።

ሚስቱም በአላህ ይሁንብኝ እራሱ አቡ ሚህጀን ነው ብላ የተከሰተውን አስረዳችው። በሁኔታው በእጅጉ የተደሰተው ሰዕድ አቡ ሚህጀንን አስጠርቶ ከዛሬ ጀምሬ አልገርፍህም። አላስርህም በነፃ ለቅቄሀለው አለው።

አቡ ሚህጀንም እንግዲያውስ እኔም ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም አልሰክርም በማለት መለሰ።

ረድየላሁ አንሁም አጅመዒን

#mahi mahisho

ቴሌግራም

👇👇👇

t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

ኡማ ላይፍ

👇👇👇

https://ummalife.com/mahimahisho

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group