Translation is not possible.

በታሪክ ትልቁ ይቅርታ

...

አቡ ዘር ቢላልን ‹አንተ የጥቁር ልጅ!› አለው፡፡

ቢላል በአቡ ዘር ንግግር ተቆጣ፣ አዘነም፡፡ ይህን ጉዳይ ለአላህ

መልዕክተኛ ነው የምናገረው በማለት ወደርሣቸው ሄደ፡፡

በሰሙት ነገር የአላህ መልዕክተኛ ፊት ተለዋወጠ፡፡ እንዴት

በእናቱ ታነውረዋለህ፣ ገና የመሃይምነት ቅሪት ከዉስጥ

አልወጣም፡፡› አሉት፡፡ ለአቢ ዘር፡፡

አቢ ዘር የሠራው ስህተት ከባድ መሆኑ ታወቀው፡፡ አለቀሰ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ‹አጥፍቻለሁ ምህረት ይለምኑልኝ!›

አላቸው፡፡

እያለቀሠም ከመስጂዱ ወጣ፡፡

አቡ ዘር ሄደና ቢላል እግር ሥር ወደቀ፡፡ ጉንጩንም ከአፈር አገናኘ፡፡

‹አንተ የተከበርክ፤ እኔ ወራዳ ነኝ፡፡ በእግርህ ፊቴ ላይ ካልቆምክ በስተቀር አልነሳም› አለው፡፡

ቢላልም እንዲህ አለ ‹ በአላህ እምላለሁ፤ ለአላህ ብላ ሱጁድ ያደረገች ፊት ላይ አልቆምም፡፡›

አቡ ዘር ከተደፋበት ተነሳ፡፡ ተቃቅፈው አለቀሱ፡፡ ይቅር ተባባሉ፡፡

በወንድሞቻችን ላይ ስንቴ ድንበር አልፈናል! ስንቴስ አጥፍተናል!፡፡

ስላጠፋነው ጥፋት ይቅርታ ጠይቀን እናውቅ ይሆን!!

ዘረኝነት ክፉ ደዌ ነው!

Send as a message
Share on my page
Share in the group