Translation is not possible.

አንድ ትንሽዬ ልጅ ለወላጆቹ፦"3 ጥያቄዎቼን የሚመልስልኝ

ጠንካራ ዑለማ አምጡልኝ" አላቸው።

ወላጆቹም በአከባቢያቸው ያለ አንድ ኡስታዝ አመጡለትና

አገናኙት።

💧ልጁ፦"ማን ነህ አንተ? እኔ ስለምጠይቀውስ ጥያቄ መልስ

እንዳለህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ?"

➣ኡስታዙ፦"ስሜ ዐብዱላህ ይባላል ከአላህ ባሪያዎችም አንዱ

ነኝ።ለምትጠይቀኝ ጥያቄዎችም በአላህ ፍቃድ መልስ

እሰጥሀለሁ።"

💧ልጁ፦"አንተ ግን ብዙ ዑለማኦች ሊያብራሩልኝ ያልቻሉትን

ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነህ?

➣ኡስታዙ፦"ልመልስልህ እሞክራለሁ በአላህ እገዛ።"

💧ልጁ፦" 3 ጥያቄዎች አሉኝ።

❶ ➛ እውነት ፈጣሪ አለ? አዎ አለ የምትል ከሆነ አሳየኝ የት ነው

ያለው?

❷ ➛ ቀዷ እና ቀደር ምንድነው?

❸ ➛ እውነት ሸይጣን ከእሳት የተፈጠረ ከሆነ እንዴት በእሳት

ይቀጣል? ከእሳት ተፈጥሮ እሳት አያቃጥለውም።

"ይሄን ግዜ ኡስታዙ እሳት በሆነች ጥፊ ልጁን አጮለው።

💧ልጁ፦"እንዴ!!! ለምን ትመታኛለህ? ምን ሚያስመታ ነገር

ተናገርኩ?

➢ኡስታዙ፦"አረ!!! እኔ አልተቆጣሁም ግን ያሁኗ ጥፊ ለሶስቱም

ጥያቄዎችህ መልስ ናት።

💧ልጁ፦"እንዴት? አልገባኝም...

➢ኡስታዙ፦"በጥፊ ስመታህ ምን ተሰማህ?

ልጁ፦"በጣም ህመም ተሰማኝ።

➢ኡስታዙ፦"ህመም እንዳለ ታምናለህ?"

💧ልጁ፦"አዎ አምናለሁ።"

➢ኡስታዙ፦"አሳየኝ የት ነው ያለው?"

ልጁ፦"አይ አለ ግን ማየት እንኳን አይቻልማ"

➢ኡስታዙ፦"ይህ ለመጀመሪያ ጥያቄህ መልስ ነው።ሁላችንም

አላህ እንዳለ እናምናለን ነገር ግን ማየት አንችልም።

እሺ ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ ገምተህ ነበር?"

ልጁ፦"አልገመትኩም።"

➢ኡስታዙ፦"እሺ እኔስ አንተን ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ አስቤ

ነበር?

💧ልጁ፦"አላሰብክም።"

➢ኡስታዙ፦"ለ2ኛ ጥያቄህ መልስ ይህ ነው ቀዷ ቀደር

የሚባለው።

እሺ እኔ አንተን የመታሁበት እጄ 💧ከምንድነው የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"

➢ኡስታዙ፦"እሺ በእጄ የመታሁት ያንተ ፊትስ ከምንድነው

የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"

➢ኡስታዙ፦"ስመታህ ምን ተሰማህ?"

💧ልጁ፦"አመመኝ"

➢ኡስታዙ፦"ከአፈር የተሰራ አፈርን ሲመታው

እንደሚያሳምመው ሁላ ከእሳት የተሰራውም ሸይጣን በእሳት

ሲቀጣ በጣም ያመዋል።"

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group