Translation is not possible.

ታታሮች በ 1258 ባግዳድ ገብተው ከ800,000 በላይ ሙስሊሞችን ገደሉ ይህን ዘመን የታሪክ ጸሐፊው ኢብኑል አሲር እንዲመዘግብ ጠየቁት

ኢብኑል አሲር ይህ ክስተት የአለም መጨረሻ እንደሆነ እና የቂያማ ምልክቶች ናቸው ብሎ አሰበ እነዚህን አጭር አፍታዎች መመዝገቡ ምንም ፋይዳ አይኖረውም ብሎም አሰበ።

እምቢ አለና ዝነኛ አባባሉን እንዲህ አለ፡- ማን ነው? ለእስልምና እና ለሙስሊሞች የሙት መጽሃፍ (የሀዘን መጽሃፍን) መፃፍ የሚቀለው ? ለማን ይሆን ይህን ማድረግ የሚቀለው? ምነው እናቴ ባትወልደኝ፣ እናም ከዚህ በፊት በሞትኩና በተረሳሁ ምኞቴ ነበር።

ከሁለት አመት በኋላ ታታሮች በአይን ጃሉት ጦርነት በንጉስ ሙዘፈር ሰይፈዲን رحمه الله ተሸነፉ።

አላህ እንዲህ አለ👇

أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَكَانُوٓا۟ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعْجِزَهُۥ مِن شَىْءٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ إِنَّهُۥ كَانَ عَلِيمًا قَدِيرًا

በምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኀይል የበረቱ ነበሩ፡፡ አላህም በሰማያትም ኾነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና።

ጊዜ ቢፈጅም ስቃይ ቢበዛም ኢስላምና ሙስሊሞች የበላይ መሆናቸው አይቀርም❗️

ثق بالله

https://t.me/AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪና አነቃቂ የሆኑ ትምህሮችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group