Translation is not possible.

ጥቆማ‼

======

ሰሞኑን ከምታውቋቸው የቅርብ ጓደኞቻችሁ ጭምር ይህ ከታች የምትመለከቱት ሊንክ በውስጥ ተልኮላችሁ ይሆናል። ወይም በተለያዩ ግሩፖችም ላይ በርካታ ሰዎች ሲለቁት ታዝባችሁ ይሆናል።

እንደዚህ አይነት ኦፊሲያል የሆነ Domain Name የሌላቸው ሊንኮች በብዛት ከስካመሮች የሚለቀቁ ሲሆን መረጃ መመንተፊያ (ሐክ ማድረጊያ) ናቸው።

ሊንኮቹን ስትከፍቷቸው እናንተ ባታስቡትም አውቶማቲካሊ ፓስወርዳችሁንና መሰል ግላዊ መረጃዎቻችሁን ወደነርሱ ስለሚሞሉት በዛው ትዘረፋላችሁ።

አንዳንድ ጊዜ እንዳይነቃባቸው ሊንክን (URLን) በማሳጠሪያ ድረ ገፆችና አፖች ያሳጥሩትና ያሰራጩታል። እንዲህ አይነት ነገሮች በባህሪያቸው ሰውን ማማለያ ዘዴ አላቸው። ከሊንኮቹ አጠገብ ሊንኮቹን እንድትከፍቷቸው የሚገፋፋ ወስዋሽ መልዕክት ያካትቱበታል። ይሄንን ሊንክ ቢያንስ በስልክህ ላይ ለሚገኙ 100 ሰዎች ወይም ሺዎች ወይም የሆነ መጠን ይጠሩና መጀመሪያ ለነዚያ ሰዎች አሰራጭና ይሄን ያክል ሺህ ብር/ዶላር፣ ወይም የስልክ ሽልማት ወይም መኪና ወይም ላፕቶፕ ትሸለማለህ ይላሉ። ለማስመሰልም መጀመሪያ ሊንኩን ካሰራጨህ በኋላ ይሄንን ፎርም ሙላ ብለው ፎርምም ሊኖረው ይችላል።

የኛም ህዝብ እንደምታውቁት ኑሮም ስለተወደደ፣ ስራም ስለጠፋ፣ ገቢም ስላነሰ እውነት መስሎትና እድሉ የተከፈተለት መስሎት ይከፍትና ያለውን ያጣል።

አንዳንዶቹ ደግሞ ሊንክ ባይልኩም ይሄን ያክል ብር ሽልማት ልታገኙ ስለሆነ ግን ቅድሚያ ይሄነ መክፈል አለባችሁ ብለው የሚሸውዱ አሉ። የሚያሳዝነው ሁሉ አጭበርባሪ የሆነ ያክል የሚሸውደው ሰው አያጣም። ለማንኛውም ገንዘብ ዝም ብሎ በነፃ ስለማይገኝ እንዲህ አይነት ነገሮችን እያመናችሁ እንዳትሸወዱ። ለራሳችሁ ተሸውዳችሁም የምትልኩላቸውንም ሰዎች አትሸውዱ። በተለይ አንዳንዶች የሚያውቁት ሰው ሲልክላቸው ያምናሉ።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group