Translation is not possible.

ሰሞኑን አሜሪካንን ጨምሮ በምዕራባውያን ሀገራት ላይ እየተደረጉ በሚገኙት ፡ የፍልስጤማውያንን መጨፍጨፍ በሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ከተሰሙት መፈክሮች ውስጥ ፡ ይህ ከታች ያለው ግጥማዊ መፈክር ይገኝበታል!

Hey Biden, what do you say

How many kids have you killed today?

Netanyahu, you can't hide

We charge you with genocide!

By the millions , by the billions

We are all Palestinians!

ዛሬ ላይ የአይሁዱ የእስራኤል መንግስት በንፁሐን የፍልስጤም ህፃናት ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ የአለማችን ክፍል ላይ እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይህን የህዝብ ጩኸትን ሰምቶ የአይሁዱ የእስራኤል መንግስት ወደ ልቦናው ተመልሶ የዘር ጭፍጨፋውን የማያቆም ከሆነ ፣ ይህ በመላው አለም ላይ እየተሰማ ያለው የተቃውሞ ድምፅ ወደ ጥላቻ ድምፅ እንዳይቀየር ስጋት አለኝ። ቀድሞውንም እየተቀየረ ያለም ይመስላል። በአይሁዱ የእስራኤል መንግስት የጭካኔ ተግባር ምክንያት ፡ የተለያዩ የአለማችን ህዝቦች ለአይሁዳውያን ያላቸው ጥላቻ በዚህ መልኩ እየጨመረ ከመጣ ፡ ያለፈው ታሪክ እራሱን እንዳይደግም ስጋት አለኝ። ባለፈው የአይሁዳውያን ታሪክም ከፊሎቹ አይሁዳውያን በሚያሳዩት ክፋትና ሸረኝነት ምክንያት ፣ ንፁሐኑን አይሁዳውያንን ጨምሮ በመላው የአይሁድ ህዝብ ላይ ትልቅ መሳደድና መገደል ተከስቷል። ዛሬ ላይም መላው አይሁዳውያን ካለፈው ታሪክ ተምረው የራሳቸው መንግስትን የግፍ ተግባርን ተረባርበው እራሳቸው የማያስቆሙት ከሆነ ፣ ነገ ላይ እዳው ለእነርሱም እንዳይተርፍ ስጋት አለኝ። ያለፈው ታሪክም የሚያሳየው ይህንኑ ነውና።

ስለሆነም መላው የአይሁድ ህዝቦች ፡ ስለ ፍልስጤማውያን ሲሉ ሳይሆን ስለራሳቸው ሲሉ ፡ መንግስታቸው በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም መረባረብ አለባቸው። ሐበሻ "ነግ በኔ" ብሎ የሚተርተው ለዚህ አይነቱ ክሰተት ነውና አይሁዳውያኑም ነግ በኔ ብለው የዛሬውን የፍልስጤማውያንን ስቃይ ማስቆም አለባቸው። ብልጥ ህዝብ ካለፈው ታሪኩ ተምሮ ነገውን ያስተካክላል እንጂ ፣ ያለፈውን ታሪክ ረስቶ ከዚህ በፊት ባለፈበት ታሪካዊ መከራ ውስጥ ድጋሚ በማለፍ ነገውን አያበላሽም!🙏

ይኸው ነው!🙏

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group