Translation is not possible.

➾「 ከአላህ አንቀፆች 」

✅:እነዚያ ትክክለኛ #ምዕመናን (አማኞች) እነማን ናቸው❔

➳:አላህ ﷻ ባማረ አገላለፅ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦

🔸:إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

🔹:ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት ፣ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው ፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡

🔸:الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

🔹:እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡፡

🔸:أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

🔹:እነዚያ #በእውነት_አማኞች እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረትና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡

📍| አንፋል : 2 - 4 | 📖

❛ ━━━━・❪ ማ ጠ ቃ ሊ ያ ❫・━━━━ ❜

#እነዚያ_ትክክለኛ_ምዕመናን . . .

➝¹:አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት ࿐

➝²:በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ #እምነትን የሚጨምሩላቸው ࿐

➝³:በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ࿐

➝⁴:ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ

➝⁵:ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው ፤ ይለናል ጌታችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)።

📌አላህ ከትክክለኛ ባሮቹ ያድርገን

Send as a message
Share on my page
Share in the group