Translation is not possible.

እስራኤል በጋዛ የምድር ጥቃት ከጀመረች ወዲህ 18 የእስራኤል ወታደሮች ተገድለዋል ተባለ

የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ በተካሄደው ጦርነት አንድ ሻለቃ አዛዥ መገደሉን ይፋ አድርጓል።የእስራኤል ጦር 53ኛ ሻለቃ አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ሳልማን ሃባካ የምድር ውጊያው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተገደሉት ከፍተኛ መኮንን እንደሆኑ ይታመናል። ይህም እስራኤል ወታደራዊ ጥቃትን በጋዛ ቀጠና ካሰፋች በኋላ የተገደሉትን ወታደሮች ቁጥር ወደ 18 ከፍ ያደርገዋል።

በጦርነቱ ወቅት ሌሎች አራት ወታደሮች ክፉኛ ቆስለዋል ሲል ሰራዊቱ ገልጿል። የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ባወጣው መግለጫ 9 ሺ 61 ፍልስጥኤማውያን ህይወታቸው አልፏል።ከነዚህ መካከል 3 ሺ 7 መቶ 60 ያህሉ ህፃናት ናቸው።የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት በበኩላቸው የእስራኤል ወታደሮች በሰሜናዊ ዌስት ባንክ ቃልኪሊያ አንድ ፍልስጤማዊ ሲገደሉ ሁለቱን መቁሰላቸውን ይፋ አድርጓል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በሰሜን ጋዛ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ12,000 በላይ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። የእስራኤል ጦር አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ከሊባኖስ በተተኮሰበት ቅፅበህ ከምድር ወደ አየር በሚሳኤል መመታቱን አረጋግጧል።

ግብፅ ባወጣችው መግለጫ ወደ 7,000 የሚጠጉ የውጭ አገር ዜጎችን እና ጥምር ዜጎቹን ከጋዛ ለማስወጣት እንደምትረዳ ተናግራለች። የእስራኤል የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የዲፕሎማሲያዊ ጫና እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሀገሪቱ ውሳኔ ሰጪዎች በጋዛ ውስጥ ቀስ በቀስ ለመራመድ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል ።

በስምኦን ደረጄ

#ዳጉ_ጆርናል #palestine #غزة #فلسطين #freepalestine #غزة_تحت_القصف #غزة_الآن #عاجل #فلسطين_حرة #gazaunderattack

Send as a message
Share on my page
Share in the group