Translation is not possible.

"የነጃሺ መስጂድ እና ኢስላማዊ ማዕከል"ሁለንም ያማከለ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የሚወክል ሆኖ እንድገነባ ሀሳብ ቀረበ!

...

(ሀሩን ሚዲያ ፦ጥቅምት 22/2016)

...

የታላቁ ንጉስ ነጃሺ መስጅ እና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ሂደትን አስመልክቶ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቋቋመ አብይ ኮሚቴ የነጃሺን ማዕከል ለመገንባት ከመስጅድ ባሻገር መካተት የሚገባቸው ማዕከላት ላይ ሃሳብ ለመቀበል ከተለያዩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕሌት በኤሊያና ሆቴል ውይይት አድርጓል።

...

ዛሬ በነበረው ውይይት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የየክልሉ የመጅሊስ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ኢማሞች እና ኡለሞች ምሑራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በባለሙያዎች እንዲካተቱ ከተደረጉ ማዕከላት በተጨማሪ ሌሎች እንዲካተቱ ሃሳብ ተሳጥቷል።በተለይም ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ኢስላማዊ ቅርሶች እና ሀሪማዎች ታሪኮች መገኛ በመሆኗ የሚገነባው ነጃሺ መስጂድ እና ኢስላማዊ ማዕከል ሁሉንም ያማከለ እና የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚወክል መሆን እንዳለበት ሀሳብ ተሰጥቷል።

...

የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ "በመድረኩ የተነሱትን ሃሳብ ተቀብለን ከኢንጂነሮች ጋር በመወያየት እናዳብረዋለን።" ብለዋል

...

ውይይቱ ከሰአት በኋላ በነበረው መርሀግብር የማዕከሉን ግንባታ ከሚከውኑት የኢንጂነሮች ቡድን እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ጋር በዕለቱ በተሰጡት ሃሳቦችና በአጀንደዎቻቸው ላይ ተወያይተዋል።

ማዕከሉ ግዙፍ መስጅድን ጨምሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ኤግዚቢሽን ማሳያ ቦታ፣ ኢስላማዊና ታሪካዊ ሙዚየም፣ ቤተመጽሐፍት፣ የወጣቶች ማዕከል ፣ ቢሮዎች፣ የእንግዳ ማረፊየ 1500 መኪና ማቆሚያ ፓርኪንግና ሌሎችም የሕዝበ ሙስሊሙ መገልገያ ተቋማት እንደሚኖረው ተነግሯል።

...

የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በቅርብ ቀናት ይጀመራል የተባለ ሲሆን ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንዳለበት ተነስቷል። شمس الدين

Send as a message
Share on my page
Share in the group