Translation is not possible.

አንብቡ ሼር አድርጉ

☞መፍትሄዉ ምንድን ነዉ ?

#ጥያቄ

☞ወጣት ነዉ ፡ ሱብሂ ሶላት መስጂድ ሄዶ በጀመዐ ለመስገድ ይሞክራል ፡

ችግሩ ፦ ከእንቅልፉ ይነሳና ነገር ግን መቆም ይከብደዋል

☞መፍትሄው ምንድን ነዉ ።

#መልስ

☞ለዚህ ለጠያቂው ወንድሜም ይሁን እንደሱ አይነት ላሉ ሰዎች ምክሬ ፡ በጊዜ እንዲተኛ ነዉ ፡ ከዛ በሇላ በሚነሳ ጊዜ በፍጠነት [ከአልጋዉ] ላይ ይቁም

☞ምክንያቱም ፦ኢማም ሙስሊም በሶሂሀቸዉ ላይ በዘገቡት ሀዲስ

አዒሻ [ረዲየሏሁ አንሀ] ስለ ረሱል [ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] የእንቅልፍ አነሳስ ስትናገር እንዲህ አለች ፦ [#በፍጥነት ይቆማሉ]

ይህን የአዒሻን ንግግር የዘገበዉ ሰዉ ሲናገር እንዲህ ይላል ፦ [ወላሂ አዒሻ #ይቆማሉ አይደለም ያለችዉ ፡ እሷ ያለችዉ #በፍጥነት_ይቆማሉ]

☞አንተም ከእንቅልፍ የሚያነሳህን [አላርምህን] ስትሰማ በፍጥነት ቁም ፡ አንተ በአሏህ ታግዘህ በፍጥነት ከቆምክ አሏህም ያግዝሀል ።

☞ሸይኽ ኢብን ኡሰይሚን [አሏህ ይዘንላቸዉ]

ምንጭ ☞አሊቃዑ አሻህሪይ [3]

✍አቡል ቡኻሪ ኡመር ባህረዲን

Send as a message
Share on my page
Share in the group