Translation is not possible.

ሰሜን ኮሪያ ለሀማስ መሳሪያ ልታቀርብ ነው!

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባለስልጣናት ለፍልስጤማውያን ድጋፍ እንዲዘጋጁ ያዘዙ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ ላሉ ታጣቂ ቡድኖች መሳሪያ ለመሸጥ እያሰቡ ሊሆን እንደሚችል የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት ዘግቧል።

ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም አንቲታንክ ሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ለሃማስ የሸጠች ሲሆን በጋዛ ጦርነት ወቅት ፒዮንግያንግ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ውጭ ለመላክ የምትሞክርበት እድል እንዳለ የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጪዎች ኤጀንሲው ከሰጠው መግለጫ በኋላ ተናግሯል።

የደቡብ ኮሪያ ጦር እንደገለጸው በጥቅምት 7 በደረሰው ጥቃት ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ላይ በመመስረት, ሃማስ የተለያዩ የሰሜን ኮሪያ መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ይመስላል ቢልም ፒዮንግያንግ ክሱን ሀሰት ብላ ውድቅ አድርጋዋለች።

@Wall street journal

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group